ቢሮው የሚያዚያ ወር ገቢ አፈፃፀሙን በጥልቀት በመገምገም በቀጣይ ቀሪ ሁለት ወራት የሚከናወኑ ተግባራቶች ላይ ጠንካራ አቅጣጫዎችን አስቀመጠ ።

ቢሮው የሚያዚያ ወር ገቢ አፈፃፀሙን በጥልቀት በመገምገም በቀጣይ ቀሪ ሁለት ወራት የሚከናወኑ ተግባራቶች ላይ ጠንካራ አቅጣጫዎችን አስቀመጠ ።

ግንቦት 14 / 2016 ዓ.ም አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ

ቢሮው የሚያዚያ ወርን ጨምሮ የ10 ወራት የገቢ ዕቅድ አፈፃፀምን አመራሮች ፣ ዳይሬክቶሬቶችና የቅርንጫፍ ሀላፊዎች በተገኙበት ያሳየውን ጠንካራና የታዩ ክፍተቶችን በጥልቀት ገምግሟል

በበጀት አመቱ የታቀደውን ገቢ በማላቀ በቀሪ ወራት በተጨባጭ ለማሳካትና ለቀጣይ በጀት አመት ለተልዕኮ ለመዘጋጀት በትኩረት ፣ በቁርጠኝነትና በተጠያቂነት መሠራት እንደሚገባም መድረኩን የመሩት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ሀላፊ አቶ አደም ኑሪ በአፅንኦት ተናግረዋል ።

ሀላፊው አያይዘውም ግምገማው ተቋሙ በከተማ አስተዳደሩ የተሰጠውን ገቢ የመሠብሰብ ተልዕኮ በበጀት ዐመቱ ማሳካት መሆኑን ጠቁመው ቅርንጫፎች ያቀዱትን ዕቅድ ከአፈፃፀማቸው ጋር በማነፃፀር እና በታዩ ክፍተቶች ላይ ያነጣጠረ ተግባር በማከናወን በቀሪ 2 ወራት ዕቅዳቸውን በላቀ ሁኔታ እንዲያሳኩ አቅጣጫም አስቀምጠዋል

መድረኩ በቅርንጫፎች በዕቅድ አፈፃፀሙ የታዩትን ጠንካራ እና ደካማ ጎኖች ፣ የተገኙ መልካም ተሞክሮዎች እንዲሁም በቀጣይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ላይ ያመላከተ ግምገማ እንደሆነ የቢሮው ሀላፊው አብራርተዋል

በከተማ ደረጃ በ2016 በጀት ዓመት 10 ወራት አጠቃላይ ከታቀደው 123.94 ቢሊዮን ብር 119.103 ቢሊዮን ብር በመሠብሰብ የዕቅዱን 96.10% ማሳካት መቻሉን ገልፀዋል ።

እንደ ገቢዎች ቢሮ በአስር ወራት አጠቃላይ ከታቀደው 89.721ቢሊዮን ብር 94.818 ቢሊየን ብር በመሠብሠብ የዕቅዱን 105.68 % ማሳካት መቻሉ በጥሩ ጎን መነሳቱን የጠቆሙት ሀላፊው እንደ አጠቃላይ ግባችንን 100++ ለማሳካት መትጋት ይኖርብናል ብለዋል

የነበረንን ጥንካሬ ማስቀጠል ፣ የታዩ ክፍተቶችን በጥልቅ በመገምገም በቀጣይ ቀሪ ወራት ሊተኮሩ የሚገባቸውን ነጥቦች በመለየት ለላቀ ገቢ አፈፃፀም በተጠያቂነት እንደሚሰራም እንዲሁም የተቋሙ የመጨረሻ መለኪያ ውጤት የገቢ ዕቅዱን ማሳካት እንደሆነ አቶ አደም አሳስበዋል ።

ቢሮው በ2016 ዓ.ም በጀት አመት በከተማ ደረጃ በበጀት አመቱ 140.29 ቢሊየን ብር ለመሠብሠብ አቅዶ ወደ ተግባር መግባቱ ይታወቃል ።

በበጀት ዐመቱ የሚያዚያ ወርን ጨምሮ የአስር ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ዙሪያ አመራሩ ፣ የቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ስራ አስኪያጆችና የቢሮው ዳይሬክቶሬቶች በተገኙበት መድረክ አፈፃፀሙን በመገምገም የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችንም አስቀምጧል።

የቢሮው የ2016 ዓ.ም የሚያዚያ ወር ዕቅድ አፈፃፀም ከተቋሙ ቁልፍና አበይት ተግባራት አንፃር አፈፃፀሙ ያሳየውን ጠንካራና ክፍተቶች ማሻሻል ያለባቸውና ማላቅ የሚገባቸውን ተግባራት እንዲሁም የቀጣይቀሪ 2 ወራት የትኩረት አቅጣጫዎች በዝርዝር በቢሮው የበጀት ፣ ዕቅድ ዝግጅት ክትትልና ድጋፍ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በአቶ ጥላሁን ግርማ ቀርቦ በዕቅድ አፈፃፀሙ ዙሪያ ጥልቅ ውይይት እና ግምገማ በተሳታፊዎቹ ተካሂዶበታል ።

መድረኩን የመሩት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ሀላፊ አቶ አደም ኑሪ እንደገለፁት የከተማ አስተዳደሩ የሰጠንን የላቀ ገቢ አሠብሰብ በተግባር ለማሳካት በቀሪ 2 ወራት በአንዳንድ ቅርንጫፎች የታዩ ክፍተቶችን በማሻሻል ወደ ገቢ በመቀየር የተሻለ አፈፃፀም እንዲመዘገብ ለቅርንጫፎች ተጠያቂነት ያለው የስራ መመሪያና አቅጣጫ ሰጥተዋል ።

የቅርንጫፍ ስራ አስኪያጆች በክፍተት የታዩ ጉዳዮች ላይ ከራሳቸው ነባራዊና ውስጣዊ አሰራር አንፃር በመፈተሽ በተጠያቂነትና ክፍተቱን ፈቺ የሆነ ዕቅድ በቀሪ 2 ወራት በመከለስ የበጀት ዐመቱን የገቢ ዕቅድ አሰባሰብ ለማሳካት በትኩረትና በተጠያቂነት እንደሚሰሩ በግምገማዊ መድረኩ ላይ ገልፀዋል ።

በግምገማዊ ውይይቱ ላይ ለተነሱ ሀሳቦችና ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ከየዘርፉ ሀላፊዎችም ተሰጥቶበታል ።

#ውጤታማ_የገቢ አሰባሰብ ፣ ለአዲስ አበባ ብልፅግና !

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *