የሶማሌ_ክልላዊ_መንግስት ገቢዎች ቢሮ የገቢ አቅማቸውን ለማሳደግና አሰራሮችን ለማዘመን ከከተማ አስተዳደሩ ገቢዎች ቢሮ ጋር የሁለትዮሽ የስራ ልምድ ልውውጥ መድረክ ተካሄደ ።

  · 

#የሶማሌ_ክልላዊ_መንግስት ገቢዎች ቢሮ የገቢ አቅማቸውን ለማሳደግና አሰራሮችን ለማዘመን ከከተማ አስተዳደሩ ገቢዎች ቢሮ ጋር የሁለትዮሽ የስራ ልምድ ልውውጥ መድረክ ተካሄደ ።

ግንቦት 16 / 2016 ዓ.ም አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ

ከሶማሌ ክልላዊ መንግስት ገቢዎች ቢሮ የተውጣጡ አመራሮች የክልሉን የገቢ አቅም ለማሳደግና ዘመናዊ የገቢ አሰባሰብ ስርዐትን ለማስፋት ፣ የከተማዋ የታክስ አሰባሰብ ፣ መሪ ዕቅድ ፣የገቢ ክትትልና ቁጥጥር ድጋፍ ፣ የተጨማሪ የገቢ አሰባሰብ ፣ የታክስ ምርመራ ፣ የቴክኖሎጂ አጠቃቀምና የገቢ ማስፋት ጋር በተያያዘ ልምድ ለመውሰድ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ጋር በቼክ ሊስት ዝርዝር የመረጃ ልውውጥ አካሂደዋል ።

የልዑካን ቡድኑን በፅህፈት ቤታቸው ተቀብለው ያነጋገሩት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ሀላፊ አቶ አደም ኑሪ እንደገለፁት ” የሶማሌ ክልል የገቢ ቢሮ አመራሮች ” የፍቅር ፣ የሰላምና የአብሮነት ከተማችሁ ወደ ሆነችው አዲስ አበባ እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት ደስታቸውን ገልፀዋል ።

ከተማዋ ዛሬም ዘመናዊነትንና ቴክኖሎጂው የደረሰበትን አሰራር በመዘርጋት ኢኮኖሚዋ የሚያመነጨውን ገቢ በማስፋትና በአግባቡ በመሠብሰብ ልማቷን በማፋጠን አዲስ አበባ የብልፅግና ተምሳሌት መሆኗን በተጨባጭ እያሳየች መሆኑን የጠቆሙት የቢሮው ሀላፊው ክልሉ ብዙ ልምዶችን በተሞክሮነት ከመዲናችን አዲስ አበባ መቅሰም ይቻላል ሲሉ ገልፀዋል ።

አዲስ አበባ ባለፉት አመታት በገቢ አሰባሰቡ ረገድ እምርታ ማሳየቷን የገለፁት አቶ አደም ዘንድሮም ያቀድነውን በተግባር ለማሳካት ዘመናዊና ቴክኖሎጂን መሠረት ያደረገ የገቢ አሰባሰብ ስርዐትን በቁርጠኝነትና በተጠያቂነት አሰራር እየተገበርን ነው ሲሉ በዝርዝር ለልዑካኑ አባላት አብራርተውላቸዋል ።

የክልሉ ገቢ ልዑካን በቆይታቸው መልካሙን ሁሉ እንዲገጥማቸው የተመኙት ሀላፊው በቀጣይም ክልሉ በገቢ አሰባሰቡና በሁለንተናዊ የለውጥ ጎዳናው እንዲሳካላት የከተማ አስተዳደሩ ገቢዎች ቢሮ ባለው አቅም ሁሉ ድጋፉና የልምድ ልውውጥ እንደማይለያቸው ገልፀዋል ።

የሶማሌ ክልል መንግስትገቢዎች ቢሮ ልዑክ ከክቡር ቢሮ ሀላፊው ጋር በነበራቸው ቆይታና በተደረገላቸው ገለፃ የተደሰቱ መሆናቸውን አመሥግነው ባቀረቡት ቼክ ሊስት መሠረት መረጃ ማግኘታቸውን የሶማሌ ክልላዊ መንግስት ገቢዎች ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ አብዲቃድር መሀመድ ሹግሪ ለዝግጅት ክፍላችን ገልፀዋል ።

አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ በቼክሊስት በተዘጋጀ የመረጃ ልውውጥና የልምድ ተሞክሮ ማካፈሉ ለክልላችን ገቢ ማደግ ወሳኝነት አለው ብለዋል ።

በቆይታቸው የተደሰቱት የክልሉ ገቢ ቢሮ አመራሮች ለክልሉ የገቢ አሰባሰብ መሠረት የሚሆኑ ልምዶችን ፣ገለፃዎችንና ተሞክሮዎቹን ከአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ማግኘታቸውን ገልፀው በቀጣይም በክልሉ ቢሮው ተገኝቶ አስፈላጊውን ድጋፍም እንደሚያደርግላቸውም ያላቸውን ምኞት ከወዲሁ ገልፀዋል ።

#ውጤታማ_የገቢ አሰባሰብ ፣ ለአዲስ አበባ ብልፅግና !

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *