የቢሮው የታክስ ውሳኔ ቅሬታ አጣሪ ዳይሬክቶሬት ለዘርፉና ለሚመለከታቸው ባለሙያዎች ሲሰጥ የቆየው የአቅም ግንባታ ስልጠና ተጠናቀቀ ።

የቢሮው የታክስ ውሳኔ ቅሬታ አጣሪ ዳይሬክቶሬት ለዘርፉና ለሚመለከታቸው ባለሙያዎች ሲሰጥ የቆየው የአቅም ግንባታ ስልጠና ተጠናቀቀ ።

ግንቦት 17/ 2016 ዓ.ም አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ

በ IFRS, Asset valuation እና Finanical Modeling ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ስልጠና ለ5 ተከታታይ ቀናት ለዋና ቢሮ የታክስ ውሳኔ ቅሬታ አጣሪ ከፍተኛ ባለሙያዎች፣ ለቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች የታክስ ውሳኔ ቅሬታ አጣሪ ከፍተኛ ባለሙያዎች ፣የስራ ሂደት አስተባባሪዎች ፣ለውስጥ ኦዲትና ለስነ-ምግባር የስራ ክፍል ሰራተኛች በድምሩ ለ110 ተሳታፊዎች ስልጠናው ተሰጥቷል ።

በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ሀላፊ አቶ አደም ኑሪ እንደገለፁት ” በስራ ላይ የሚሰጡ አቅም መገንቢያ የሆኑ ስልጠናዎች የበለጠ ክህሎትን በማሳደግ የታቀደውን ገቢ በተሳካ ሁኔታ ለመፈፀም ያስችላል ብለዋል ።

ሰልጣኞች በስልጠና ያገኛችውትን ዕውቀት በስራ ላይ በመተግበር ፣ ለሌሎች የስራ አጋሮቻችው በማካፈልና በታማኝነት ውጤታማ ስራ እንድትሰሩ አደራ ያሉት ቢሮ ሀላፊው ስልጠናውን ለሰጠው ተቋም ምስጋናቸውን በቢሮውና በራሳቸው ስም አቅርበዋል ።

በአዲስ አበበ ገቢዎች ቢሮ የታክስ ውሳኔ ቅሬታ አጣሪ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወይዘሮ ወይንሸት ፀጋዬ በበኩላቸው የስልጠናውን ዐላማ እንደገለፁት ” በተቋም ግንባታ ላይ መሠረት አድርጎ የሰራተኛን አቅም ለመገንባትና የተሻለ አፈፃፀም ገቢ አሰባሰብና አገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል እንዲሁም ወጥ የሆነና የተናበበ የአሰራር ሂደት እንዲኖር ለማድረግ መሆኑን ገልፀዋል ።

ስልጠናው በንድፈ ሀሳብና ሰልጣኞችን ባሳተፈ መልኩ መካሄዱን የገለፁት ወይዘሮ ወይንሸት ይህን መሠል ስልጠናም በቀጣይነት በታክስ ህግ ፣ አዳዲስ በሚወጡ መመሪያዎች እና አፈፃፀም ዙሪያ ተከታታይነት ያለው ስልጠና ለመሥጠት መታቀዱንም አብራርተዋል ።

በ IFRS, Asset valuation እና Financial Modeling ዙሪያ ለሰልጣኞች ስልጠናውን የሰጡቱከipass consultancy and Trainingየመጡ የዘርፉ ባለሙያዎች ሲሆኑተቋሙ ለ5 ቀናት ለሰጠው የአቅም ግንባታ ስልጠናና ድጋፍ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የምስጋና የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል

በስልጠናው የተሳተፉ ስልጣኞችም በቆይታቸው ለስራቸው አጋዥ የሆነና አቅም የፈጠረ ፣ ለበለጠ ውጤታማነት የሚያነሳሳና የሚያነቃቃ ሙያዊ ክህሎትን የሚያሳድግ ስልጠና በማግኘታቸው መደሰታቸውን ገልፀዋል ።

ለአምስት ተከታታይ ቀናት ስልጠናቸውን ተከታትለው ለጨረሱ ሰልጣኞች የተዘጋጀላቸውን የምስክር ወረቀት ከዕለቱ የክብር እንግዳ ከቢሮ ሀላፊው እጅ ተቀብለዋል ።

ውጤታማ የገቢ አሰባሰብ ፣ ለአዲስ አበባ ብልፅግና!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *