የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ Addis Ababa Revenues Bureau
5.94K subscribers
10.1K photos
150 videos
9 files
1.01K links
Download Telegram
የታክስ ቅጣት ውሳኔዎችን በማንሳትና የግብር ከፋዩን ጥያቄ በመመለስ ግብር ከፋዩ በንግድ ስርዓት ውስጥ እንዲቆይ ከማድረግ አኳያም በርካታ ተግባራት መከናወናቸውን ደግሞ የገለፁት አቶ ንብረት በሪሁን የታክስ ዕዳ  አስተዳደር ዳይሬክተር  ሲሆኑ በዚህም
ባለፉት ስድስት ወራት የ262 ግብር ከፋዮች ቅጣት ይነሳልኝ አቤቱታ በማድመጥና መረጃዎችን በመመርመር ከ579 ሚሊዮን ብር በላይ ቅጣት ማንሳቱንም አብራርተዋል።

ከዚህም ባሻገር ለ170 ግብር ከፋዮች ከ6-24 ወራት የጊዜ ስምምነት በመስጠትም ተገቢው ድጋፍ መደረጉምንም ጠቁመዋል።

በመጨረሻም ቢሮው ግብር ከፋዮች የታክስ ውሳኔ ቅሬታ ካላቸው የሚፈታበት ስርዓት በመዘርጋት እየፈታ መሆኑን በመገንዘብ በተዘረጋው አሰራር ብቻ በመጠቅም ቅሬታዎቻቸውን እንዲያቀርቡም ጥሪ ቀርቧል።

ውጤታማ የገቢ አባሰብ ለአዲስ አበባ ብልጽግና
👏2
የመንገድ ግንባታ በሚከናወንባቸዉ አካባቢዎች ተሽከርካሪዎችን አቁሞ መሄድ ተከለከለ

ጥር 04 / 2018 ዓ/ም አዲስ አበባ ።

የመንገድ ግንባታ በሚከናወንባቸዉቦታዎች ተሽከርካሪዎችን አቁሞ መሄድ የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ የኮሪደር ልማትና የመንገድ ግንባታ በሚደረግባቸው ከቅዱስ ኡራኤል፣ በአትላስ ሆቴል ኤድሞል እስከ ቦሌ ብራስ ድረስ፣ እንዲሁም አደይ አበባ ስታዲየም፣ አካባቢዎች የሚቆሙ ተሽከርካሪዎች በመንገድ ስራው ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እያሳደሩ መሆኑን ፖሊስ አስታዉቋል፡፡

በመሆኑም ከጥር 04 ቀን 2018 ዓ/ም ጀምሮ በተጠቀሱት አካባቢዎች ላይ የግንባታ ስራውን ከሚያከናውኑት ተሽከርካሪዎች በስተቀር ለአጭርም ሆነ ለረጅም ሰዓት ተሽከርካሪን አቁሞ መሄድ ፈፅሞ የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ያወጣው በ መረጃ ያሳስባል፡፡

#ውጤታማ _የገቢ_አፈፃፀም ፣ ለአዲስ አበባ ብልፅግና !!
"የአዲስ አበባ ወንዞች ትንሣኤ"

ዛሬ ምሽት 2 :30 ይጠብቁን
ኢትዮጵያን አፍሪካዊት የብልፅግና ተምሳሌት እናደርጋለን የሚለው ራዕይ በትክክለኛ አቅጣጫ ላይ ስለመሆኑ ውጤቶቻችን ማሳያ ናቸው- የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር እናታለም መለሰ

እንደ ሀገር ጥራት ያለው የኢኮኖሚ ዕድገትንና የጋራ ብልፅግናን የሚያረጋግጥ ስራዎችን እንዲሁም አካታችና ዘላቂ የኢኮኖሚ ዕድገት የሚያረጋግጥ የብዝሃ ዘርፍ የልማት ስትራቴጂ በመከተል እየሰራናቸው ያሉ ስራዎች በሁሉም መስኮች ፍሬ እያፈሩና የኢትዮጵያን በ2023 አፍሪካዊት የብልፅግና ተምሳሌት እናደርጋለን በሚል የተነሳንለትን አላማ በሚያሳካ ትክክለኛ አቅጣጫ ላይ መሆናችንን ያረጋገጠ ነው ሲሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር እናታለም መለሰ አስታወቁ፡፡

የኢፌድሪ መንግሥት የኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ወ/ሮ እናት አለም መለሰ ለተለያዩ የሚድያ አካላት የተከናወኑ ዋና ዋና መንግሥታዊ ሥራዎችን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በቢሾፍቱ አቡሴራ የግንባታ ሥራው የጀመረው የአየር ማረፊያ ፕሮጀክት፣ የታላቁ ህዳሴ ግድብ መጠናቀቅ፣ እና ሌሎች ሀገራዊ ግዙፍ ፕሮጀክቶች የኢትዮጵያ ማንሰራራት ዘመን ማሳያዎች እንደሆኑ ጠቁመዋል፡፡

በተለይም ብዝኃ ዘርፍ ኢኮኖሚን ለመገንባት ኢትዮጵያ በጀመረችው እንቅስቃሴ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ዕድገት በአህጉራችን ከቀዳሚዎቹ ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት ከሚያስመዘግቡ ሃገራት ተርታ መሰለፉን አንስተዋል፡፡
መንግሥት የኢኮኖሚ ማሻሻያ መርሐ-ግብር ተግባራዊ ካደረገባቸው ጊዜያት አንስቶ የኢኮኖሚ ማነቆዎችን በየጊዜው እየፈታ እንደሚገኝ እና ፡ይህም የምርት አቅርቦትን፣ የመንግሥት ገቢን፣ የውጭ ምንዛሬ ክምችትን እና የወጪ ንግድን ማሳደግ መቻሉን ሚኒስትሯ ገልፀዋል፡፡

የዋጋ ግሽበትን በመቆጣጠር ፣ግብርናን ማዘመንና በማሻሻል፣ የአምራች ኢንዱስትሪውን ለፈጠራና ለፍጥነት ዕድገት ምቹ የሆነ ማዕቀፍ መፍጠር ፣በማዕድን ዘርፍ ሀብቶቻችንን ማወቅ፣ መግለጥና ለኢትየጵያ ብልፅግና ማዋል እንዲሁም በቱሪዝም   ነባር ሀብቶቻችንን "ማስተካከል፣ ማስፋትና ማበርከት" በሚለው መርህ በመመራት የዛሬን ብቻ ሳይሆን የነገን የትውልድ ቀጣይነት  እየተገነባባቸው መሆኑን  ተናግረዋል፡፡

በዲጂታል ኢኮኖሚና የከተማ ልማት ሥራዎችም አስደናቂ ውጤት  የተመዘገበባቸው የኢትዮጵያን ተስፋ እና አቅም ያሳዩ መሆኑን ሚኒስትሯ  በመግለጫቸው አንስተዋል፡:

የያዝነው ዓመት ኢትዮጵያ ሁለት ታላላቅ ሁነቶች፡ ጠንካራ ሀገራዊ መግባባትን ለመፍጠር የሚረዳ ሀገራዊ ምክክር እና የ7ኛውን ዙር ሀገራዊ ምርጫ የምታካሂድበት መሆኑም በመግለጫው ተካቷል፡፡
የመደመር መንግሥት ሀገራዊ ምክክሩ አካታች እና ውጤታማ ምርጫውም ፍጹም ሰላማዊ፣ ፍትሃዊ፣ ገለልተኛ እና ተዓማኒነት ያለው ሆኖ እንዲጠናቀቅ ለማስቻል በቁርጠኝነት እንደሚሰራ መግለጫው በአጽንኦት  ገልጾአል፡፡

በመጨረሻም፣ የተመዘገቡት ውጤቶች የመደመር መንግሥት ሕዝብ የተሳተፉበት አካታች የልማት እሳቤን በመከተል ፈጣን ሀገራዊ እድገትን ፣ በአህጉር እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ደግሞ የኢትዮጵያን ስትራቴጂካዊ የዲፕሎማሲ ልዕልናን ወደላቀ ደረጃ ለማድረስ በሁሉም ዘርፎች እየሰጠ የመጣው ወሳኝ አመራር ውጤት መሆኑንም መግለጫው አመላክቷል፡፡
በፒያሳ እና አካባቢዉ የተገነቡ የወንዝ ዳርቻ ልማት ሥራዎች ለአዲስ አበባ አዲስ ገጽታ አላብሰዋታል ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ

በፒያሳ እና አካባቢዉ የተገነቡ የወንዝ ዳርቻ ልማት ሥራዎች ለአዲስ አበባ አዲስ ገጽታ አላብሰዋታል ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለመዲናዋ አዲስ ገጽታ ያላበሱትን በፒያሳና አራዳ አካባቢ የተገነቡ የወንዝ ዳርቻ ልማቶችን ተዘዋዉረዉ በመጎብኘት ገለጻ አድርገዋል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ እንደገለጹት፤ አራዳ ፓርክና ፒያሳ አዲስ አበባን እንደ አዲስ በሚያሳይ ከፍታ በአጭር ጊዜ ተገንብተዋል።

ይህ ለውጥ የከተማዋን ውበት ብቻ ሳይሆን የማንነት መገለጫ ጭምር ሆኗል ነው ያሉት።

በከተማዋ የለሙ የወንዝ ዳርቻዎች የወንዙን ተፈጥሯዊ ፍሰት ሳይገቱ፣ ከሥነ-ምህዳሩ ጋር በተስማማ መልኩ ለአይን በሚማርክ ውበት መገንባታቸውን ገልጸዋል።

ቀደም ሲል በአካባቢው የተገነባ ህንጻ እምብዛም አለመኖሩን አስታውሰው፤ አሁን ላይ አዳዲስ ህንጻዎች ተገንብተው ለከተማዋ ተጨማሪ ድምቀት መሆናቸውን ተናግረዋል።

ህንጻዎቹ ከወንዞችና ከተፈጥሮ ጋር ተስማምተው ሲታዩ መንፈስን ያድሳሉ ያሉት ከንቲባ አዳነች፤ ከዚህ የተነሳ ፕሮጀክቶቹ በይፋ ሳይከፈቱ ነዋሪዎች እየተዝናኑበት እንደሆነ ገልፀዋል።

እነዚህ ፕሮጀክቶች ለነዋሪዎች የመንፈስ እርካታ ከመፍጠራቸው ባሻገር አዲስ አበባን የዘመናዊነት ማዕከል አድርገዋታል።

አካባቢውን የሚያሳምሩና ለነዋሪዎች ምቹ የሆኑ አዳዲስ መንገዶች መገንባታቸውም ተዳማሪ ድምቀት መሆናቸውን ገልጸዋል ።
2
በአጥር ተከልሎ የመኖር አሮጌ ባህል ቀርቶ፣ የጋራ መጠቀሚያ ሥፍራዎችን በማስፋፋት ዘመናዊ የከተማ አኗኗር እንዲስፋፋም ተደርጓል።

ይህ ስኬት የመንግስት፣ የግሉ ዘርፍ እና የአልሚዎች የጋራ ጥረት ውጤት መሆኑን ከንቲባ አዳነች ገልጸው ለተሳትፎቸውም ምስጋና አቅርበዋል።

ወቅታዊ_እና_የተሟሉ_መረጃዎችን_ለማግኘት፡-
#በድረ-ገጽ_እና_ማኅበራዊ_ሚዲያ፡-
ድረ ገጽ፦ www.aarevenuesbureau.gov.et
   ቴሌግራም፦ https://t.me/aarevenues
   ቴሌግራምhttps://t.me/aacarb/1
   ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/share/p/17D365kZtf/
   ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/@addisababarevenuesbureau
   ቲክቶክ፡- tiktok.com/@addis.ababa.revenue
   ኢንስታግራም:- https://www.instagram.com/stories/addisababarevenue
   Linkedin:- https://www.linkedin.com/.../addis-ababa-revenues-bureau...
   imo https://www.imo.com.addis ababa revenues bureau
#በቴሌቪዥን_ፕሮግራሞቻችን፡-
ፋና ቴሌቪዥን እሁድ ማታ ከ1፡30 ዜና በኋላ፣
ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን /ኢ.ቢ.ሲ/ ሰኞ ማታ ከ3፡00 ዜና በኋላ፣
#በሬድዮ_ፕሮግራሞቻችን፡-
አዲስ ሚዲያ ኤፍ ኤም ሬድዮ 96.3 ማክሰኞ ከ5:00 - 6:00፣
#በወርሃዊ_ጋዜጣችን_እና_ነጻ_ጥሪ_አገልግሎት፡-
ገቢያችን ህልውናችን ወርሃዊ ጋዜጣ እንዲሁም  በነጻ ጥሪ አገልግሎታችን፡- 7075 ላይ በነፃ በመደወል መረጃዎችን መጠየቅ ይችላሉ።
2
ታዋቂው የአለማችን ዩቲዩበር እና የቀጥታ ስርጭት አቅራቢዉ አይሾው ስፒድ አዲስ አበባን እየጎበኘ ነዉ

ታዋቂው አሜሪካዊዉ ዩቲዩበር እና የቀጥታ ስርጭት አቅራቢዉ ወጣት አይሾው ስፒድ ወይም ዳረን ዋትኪንስ ጁኒየር አዲስ አበባን በመጎብኘት ላይ ይገኛል፡፡

በፈረንጆቹ አቆጣጠር ጥር 21 ቀን 2005 በኦሃዮ አሜሪካ የተወለደዉ ዳረን ዋትኪንስ ጁኒየር በዩቲዩበር ፣ ስትሪመር እና ራፐር ሙያዎቹ በአለም ላይ በስፋት ይታወቃል፡፡

አይሾው ስፒድ በቪዲዮዎቹ ላይ በሚያሳየው ከፍተኛ ጉልበት ፣ ድንገተኛ ጩኸት እና አስቂኝ ድርጊቶች ይታወቃል።

አይሾው ስፒድ በቲክቶክ ላይ በሚለቃቸዉ የራሱ አጫጭር ቪዲዮዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ በአጭር ጊዜ ዉስጥ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተከታዮችን አግኝቷል።

አይሾው ስፒድ በአሁኑ ወቅት "Speed Does Africa" የተሰኘ ጉዞ እያደረገ ሲሆን፣ ኢትዮጵያን ጨምሮ በርካታ የአፍሪካ ሀገራትን እየጎበኘ ይገኛል።

በኬንያ በነበረው ቆይታ በአንድ ቀን ውስጥ ብቻ ከ300 ሺህ በላይ አዲስ ተከታዮችን በማግኘት የዩቲዩብ ተከታዮቹን ቁጥር 48 ሚሊዮን አድርሷል።

በኢትዮጵያም በርካታ ዩቱዩበሮች የአዲስ አበባ ጉብኝቱን በመከታተል ላይ ናቸዉ፡፡

ከቅርብ አመታት ወዲህ በአለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ ዩቲዩበሮች፤ ቲክቶከሮች፤ ጋዜጠኞች፤ አርቲስቶች፤ የስፖርት ባለሙያዎች፤ የሃገራት መሪዎችና ቱሪስቶች ምርጫቸዉን አዲስ አበባ በማድረግ መዲናዋን ከመጎብኘታቸዉም በላይ የኢትዮጵያን መልካም ገጽታ በአለም አቀፍ ደረጃ በማስተዋወቅ ላይ ይገኛሉ፡፡
6