የቢሮው የህግ ተገዢነት ዘርፍ በየደረጃው ከሚገኙ የታክስ ሕግ ተገዢነት ዘርፍ አመራሮች ፣ ዳይሬክተሮችና ሰራተኞች ጋር የዘርፉን የ9 ወራት አፈፃፀምን በጋራ ገመገመ ።

የቢሮው የህግ ተገዢነት ዘርፍ በየደረጃው ከሚገኙ የታክስ ሕግ ተገዢነት ዘርፍ አመራሮች ፣ ዳይሬክተሮችና ሰራተኞች ጋር የዘርፉን የ9 ወራት አፈፃፀምን በጋራ ገመገመ ።

ሚያዚያ 10 / 2016 ዓ.ም አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የሕግ ተገዢነት ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ኮማንደር አህመድ መሐመድ እንደገለፁት የመድረኩ ዋነኛ ዓላማ በዘርፉ የ2016 በጀት ዐመት የ9 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ከተቋም የትኩረት አቅጣጫዎች ከተቀመጡ ግቦች በምን ያህል መጠንና ጥራት ለገቢ አሰባሰቡ ስኬት እንደተፈጸሙ በመገምገም የታዩ ጠንካራ ጎኖች ለማፅናት እና ደካማ ጎኖችን በማሻሻል በቀጣይ ቀሪ ወራት የታቀደው ዕቅድ በላቀ ደረጃ እንዲፈጸም ለማድረግ መሆኑን ገልጸዋል ።

እንደከተማ የተቀመጠው የገቢ እቅድ ለማሳካት የህግ ተገዢነትን ና የታክስ ህግን በማስፈፀም ረገድ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች እና ፈጻሚዎች እየተመዘገቡ የሚገኙ የተሻሉ አፈጻጸሞችን እንደ ግባት በመውሰድ ክፍተት የታየባቸው ስራዎችን በቀጣይ በልዩ ትኩረት አቅዶ ለማስተካከል እንዲሁም በትግልና በውጤት ለመምራት እና በቁርጠኝነት ለመፈጸም እንደሆነ ኮማንደር አህመድ አፅንኦት ሰጥተው ገልፀዋል ።

በ9 ወራት የገቢ ዕቅድ አፈፃፀም የተገኘ ውጤት ለቀሪ የበጀት ዐመቱ ዕቅድ ስኬት ወሳኝ መሆኑን የጠቆሙት ሀላፊው አፈፃፀማችንን በጥልቀት በመገምገም የቀጣዬ አቅጣጫዎች ይቀመጣል ብለዋል ።

በቀጣይ የበጀት ዐመቱ ቀሪ ወራት የታክስ ህግ ተገዢነትን ለማስፈንና ገቢን ለማላቅ በውስጥ የሚታዩ የብልሹ አሰራር ፣ የሌብነት አመለካከትና ተግባር በትግል በመምራት ግብር ላለመክፈል የሚደረጉ ጥረቶችን በማምከንና የተጠናከረ ኦፕሬሽን ስራዎችን በተጠና መልኩ በመሥራት ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት በትኩረት እንደሚሰራም አመላክተዋል ።

ከጊዜ ወደ ጊዜ በህገወጥ እንቅስቃሴ ውስጥ ያሉ ደረሰኝ የማይቆርጡ ፣ ግብር የሚሰውሩ ፣ በሀሰተኛ ደረሰኝ የሚጠቀሙ ድርጅቶችና ግለሰቦች ላይ የተግባቦት ስራ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎች ፣ የውይይት መድረኮች ከመፍጠር ባሻገር ጠበቅ ያለ የህግ እርምጃ በተጨባጭ እየተወሰደ መሆኑን የጠቆሙት ሀላፊው በቀጣይም አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል ።

ታክስ ከፋዮ ህብረተሰብ ግብር መክፈል የመልካም ዜጋ መገለጫ መሆኑን በመረዳት ግብራቸውን በህጉ መሰረት በታማኝነትና በወቅቱ አሳውቀው እንዲከፍሉ እና የዘርፉ አመራሮችና ሰራተኞች በ 9 ወራት የታዩ ክፍተቶችን በማሻሻልና ጥንካሬዎች በማፅናት ቢሮ ለመሰብሰብ ያቀደውን የላቀ የገቢ እቅድ ለማሳካት በቀሪ ወራት እንዲረባረቡ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ።

በመድረኩ የዘርፉን የተጠመረ የ9 ወራት የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት የህግ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በአቶ ሙክታር አዲሱ በዝርዝር ቀርቦ በተሳታፊዎች ውይይት ተደርጎባቸዋል

በሪፖርቱ መነሻነት የታዩትን ጥንካሬዎችን በማጎልበት የታዩ ክፍተቶችን በማረም በቀጣይ ቀሪ ወራት የህግ ተገዢነትን በላቀ ሁኔታ በመፈፀም የገቢ ዕቅዱን ለማሳካት በቁርጠኝነትና በተጠያቂነት ጭምር ዘርፉ እንደሚሰራ በግምገማ በአቅጣጫ ተቀምጧል ።

#የላቀ_ ገቢ ፣ ለከተማችን ሁለንተናዊ ብልፅግና !

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *