በ9 ወራት የተሰበሰበውን ገቢ በማላቀ በቀሪ ወራት የተቀመጠውን ዕቅድ በተጨባጭ ለማሳካት በትኩረትና በቁርጠኝነት ይሰራል

” በ9 ወራት የተሰበሰበውን ገቢ በማላቀ በቀሪ ወራት የተቀመጠውን ዕቅድ በተጨባጭ ለማሳካት በትኩረትና በቁርጠኝነት ይሰራል ።”

አደም ኑሪ

የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ሀላፊ ።

ቢሮው የ2016 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወር የእቅድ አፈፃፀም ግምገማ በማካሄድ የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫዎቹን አስቀመጠ ።

ሚያዚያ 17 / 2016 ዓ.ም አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በበጀት ዐመቱ በዘጠኝ ወራት አቅዶ ባከወናቸው ቁልፍ እና አበይት ተግባራት ከተቋሙ 5 የትኩረት አቅጣጫዎች አንፃር አፈፃፀሙን ገምግሟል ።

መድረኩን የከፈቱት የቢሮው ሀላፊ አቶ አደም ኑሪ እንደገለፁት ግምገማው ተቋሙ የተሰጠውን ገቢ የመሠብሰብ ተልዕኮ በበጀት ዐመቱ መሪ ዕቅድ ዋና ዋና ግቦችን መሠረት ያደረጉ ውጤቶች ላይ ያተኮረ ሲሆን ፣ ከአፈፃፀማቸው ጋር በማነፃፀር እና በታዩ ክፍተቶች ላያ ያነጣጠረ መሆኑን ጠቁመዋል ።

በዕቅድ አፈፃፀሙ የታዩትን ጠንካራ እና ደካማ ጎኖች ፣ የተገኙ መልካም ተሞክሮዎች እንዲሁም በቀጣይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ሊይ ያመላከተ ግምገማ እንደሆነ የቢሮው ሀላፊው አፅንኦት ሰጥተው አብራርተዋል ።

በዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈፃፀም 108 ቢሊየን ብር 98.51 በመቶ መሠብሰቡን የጠቀሱት ሀላፊው የነበረንን ጥንካሬ ማስቀጠል ፣ የታዩ ክፍተቶችን በጥልቅ በመገምገም በቀጣይ ቀሪ ወራት ሊተኮሩ የሚገባቸውን ነጥቦች በመለየት ለላቀ ገቢ አፈፃፀም በተጠያቂነት እንደሚሰራም አቶ አደም አሳስበዋል ።

ቢሮው በ2016 ዓ.ም በጀት አመት በከተማ ደረጃ በበጀት አመቱ 140.29 ቢሊየን ብር ለመሠብሠብ የታቅዶ ሲሆን በዘጠኝ ወር 109.69 ቢሊየን ብር ለመሠብሰብ አቅዶ 108.06 ቢሊየን ብር ወይም የዕቅዱ 98.51 % መሰብሰብ ተችሏል ።

በበጀት ዐመቱ የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ዙሪያ አመራሩ ፣ የቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ስራ አስኪያጆችና የቢሮው ዳይሬክቶሬቶች በተገኙበት መድረክ አፈፃፀሙን በመገምገም የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችንም አስቀምጧል

የቢሮው የ2016 ዓ.ም የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ከተቋሙ ቁልፍና አበይት ተግባራት አንፃር አፈፃፀሙ ያሳየውን ጠንካራና ክፍተቶች ማሻሻል ያለባቸውና ማላቅ የሚገባቸውን ተግባራት እንዲሁም የቀጣይ ወራት የትኩረት አቅጣጫዎች በዝርዝር ያቀረቡት በቢሮው የበጀት ፣ ዕቅድ ዝግጅት ክትትልና ድጋፍ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጥላሁን ግርማ ሲሆን በዕቅድ አፈፃፀሙ ዙሪያ ጥልቅ ውይይት እና ግምገማ በተሳታፊዎቹ ተካሂዶበታል ።

መድረኩን የመሩት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ሀላፊ አቶ አደም ኑሪ እንደገለፁት የከተማ አስተዳደሩ የሰጠንን የላቀ ገቢ አሠብሰብ በተግባር ለማሳካት በዘጠኝ ወራት የተሻለ አፈፃፀም ቢመዘገብም ተቋማዊ ግንባታን በማጠናከር ፣ ቅንጅታዊ አሰራርን በመፈተሽ ፣ የመልካም አስተዳደር ችግሮች በመፍታትና ብልሹ የሌብነት አሰራሮችን በተጨባጭ ማክሰሚያ ስልቶች በመታገል ፣ ግብር ከፋዩን በቅንነት በማስተናገድ ፣ ቀሪ ወራትን ውጤታማ ስራ ለመሥራት በቁርጠኝነትና በዝግጁነት መንቀሳቀስ ይኖርብናል ብለዋል ።

የበጀት አመቱ እቅድ በጥራት ተዘጋጅቶ በየደረጃው በማውረድ ከፈጻሚ አካላት ጋር መግባባት የደረሰበትን መሆኑንና በሪፓርቱም ዙሪያ በየደረጃው በጥልቀት የገመገመ ሲሆን በክፍተት የታዩ ጉዳዮች ላይ በተጠያቂነትና ክፍተቱን ፈቺ የሆነ ዕቅድን በመከለስ የበጀት ዐመቱን ቀሪ ወራትን ለውጤታማ የላቀ ገቢ አሰባሰብና ተቋሟዊ ግንባታ በየደረጃው እንደሚሰሩ በውይይቱቱ በስፋት ተነስቷል

በበጀት አመቱ ዘጠኝ ወራት ለታየው አፈፃፀም በየደረጃው ያሉ አመራሮች ፣ ሰራተኞች ፣ ታማኝ ግብር ከፋዮችና ባለድርሻ አካላት ጉልህ ሚና እንደነበራቸው አፅንኦት ሰጥተው የገለፁት ቢሮ ሀላፊው አሁንም የላቀ ገቢ አሰባሰቡን ለማዘመን ይበልጥ መትጋት ፣ ለቀጣይ በጀት አመትም መዘጋጀት ያስፈልጋል ሲሉ ተናግረዋል ።

በግምገማዊ ውይይቱ ላይ ለተነሱ ሀሳቦች ምላሽና ማብራሪያ ከየዘርፉ ሀላፊዎች ፣ ዳይሬክቶሬቶችና ከሚመለከታቸው አካላት ተሰጥቶበታል ።

በቀጣይ ቀሪ ወራት ያቀድነውን በማላቅ ለመሠብሠብ የተቋማት ግንባታ በሰውሀይል ፣ በአደረጃጀት እና በአሰራር ማብቃት ፣ የመሪ ዕቅድ አፈፃፀም ፣ የመልካም አስተዳደር ና የቅንጅታዊ ተቋማቶቻችን አሰራሮች መፈተሽና ለውጤት መሥራት ፣ የኢኒሼቲቭ የበጎ ተግባር ስራዎች ፣ የሌብነትና የብልሹ አሰራሮች ማክሰሚያ ሰነድ አፈፃፀሞች መገምገም ፣ መከታተልና እርምት በተጨባጭ መውሰድ ፣ ምቹ የስራ ቦታ እና ተያያዥ ጉዳዮች ትኩረት ተሰጥቷቸው የሚከናወኑ እንደሆነ የቢሮ ሀላፊው በማጠቃለያቸው አፅንኦት ሰጥተው አቅጣጫ አስቀምጠዋል ።

ምንግዜም ቢሆን የገቢያችን ዋስትና የሆኑትን ግብር ከፋዮቻችንን ፣ ማክበር ፣ ከሌብነት ነፃ ሆነን በቅንነትና በታማኝነት አሰራሩን ጠብቀን ማገልገል ፣ ሰራተኞቻችንንና ባለድርሻ አካላትን በትህትና ፣ በቅልጥፍናና በፍቅር ማስተናገድ ከእያንዳንዱ አመራርና ሀላፊ ይጠበቅብናል ሲሉም አሳስበዋል

#የላቀ_ገቢ ፣ ለከተማችን ሁለንተናዊ ብልፅግና !

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *