ቢሮው ፍትሃዊ የገቢ አሰባሰብን ለማስፈን የሚያደርገው ጥረት ውጤታማነት ለማላቅ የተቋማት ቅንጅት ሊጠናከር እንደሚገባ ተገለፀ ።
ጥቅምት 20 / 2018 ዓ.ም አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ቢሮው የበጀት አመቱን የአንደኛ ሩብ አመት የተቋማትና የባለድርሻ አካላት የቅንጅታዊ ስራዎች አፈፃፀም ግምገማ አካሄደ ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በበጀት ዐመቱ የመጀመሪያው ሩብ አመት ያቀደውን የላቀ ገቢ አሰባሰብ ለማሳካት ከባለድርሻ አካላት ጋር ቅንጅትና ትብብር በማጠናከር ያከናወናቸውን ተግባራት ዛሬ በጥልቀት በመገምገም የቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀምጧል ።…
