የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ Addis Ababa Revenues Bureau
6.09K subscribers
10.4K photos
150 videos
9 files
1.02K links
Download Telegram
በመዲናዋ በ19 ስጋ ቤቶችና በ6 የግንባታ እቃዎች መሸጫ ቤቶች ላይ በተካሄደ ኦፕሬሽን 32 ያለደረሰኝ ሽያጭ ሲፈፅሙ የተገኙ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡
ጥር 23 ቀን 2018ዓ.ም ፣ አዲስ አበባ፣ ገቢዎች ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የግብር ስወራን ለመከላከልና የንግድ ሥርዓቱን ፍትሀዊነት ለማረጋገጥና የህግ የበላይነትን ለማስከበር በተከናወነ የተጠና፣ የተቀናጀና ድንገተኛ ኦፕሬሽን በ25 የንግድ ድርጅቶች ደረሰኝ ሳይቆርጡ ግብይት ሲፈጽሙ የተገኙ 32 በስጋ ቤትና በግንባታ እቃዎች ንግድ ላይ የተሰማሩ ተጠርጣሪዎችን በህግ ቁጥጥር ስር ማዋሉን አሳወቀ።
ቢሮው ቅዳሜ ጥር 23 ቀን 2018ዓ.ም መርካቶን ጨምሮ በከተማዋ በተለያዩ አካባቢዎች ባካሄደው የተጠና የኦፕሬሽን ተግባር በ2 የንግድ ዘርፎች በድምሩ 32 የንግድ ድርጅቶች በሕግ የተጣለባቸውን የደረሰኝ አጠቃቀም ግዴታ ባለመወጣት ያለ ደረሰኝ ግብይት ሲፈጽሙ እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል ብሏል።
በዚህም ከድርጊቱ ጋር በቀጥታ ግንኙነት ያላቸው የንግድ ስራዎቹ ባለቤቶችና ሽያጩን ያለደረሰኝ ሲያከናውኑ የነበሩ ሰራተኞች የመንግስትን ግብር ለመሰወር ያለደረሰኝ ሽያጭ ሲፈፅሙ እጅ ከፍንጅ ተገኝተው በቁጥጥር ስር የዋሉ መሆናቸውን አሳውቋል፡፡
የኦፕሬሽን ተግባሩ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ጋር በመቀናጀት ማካሄዱን የገለጸው ቢሮው በቁጥጥር ስር የዋሉት ግለሰቦች የመንግሰትን ጥቅም ለማሳጣት ከታክስ አስተዳደር አዋጅ በተፃረረ መልኩ ያለደረሰኝ ሽያጭ በመፈፀም ወንጀል ተጠርጥረው በአሁኑ ወቅት ጉዳያቸው በፖሊስ ተይዞ ለፍርድ የሚቀርቡ ይሆናል ብሏል፡፡
🙏2
በቀጣይ ቀናትም ቢሮው የኦፕሬሽን ተግባሩን በሌሎችም ዘርፎች አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ያሳወቀ ሲሆን የንግዱ ማህበረሰብ ግብይቶችን በደረሰኝ ብቻ እንዲፈፅም ህብረተሰቡም በ7075 ነፃ የስልክ መስመር በመጠቀም መሰል ወንጀሎችን እንዲያጋልጥ ጥሪ አቅርቧል፡፡
ቢሮው ከዚህ ቀደም በጎማ፣ በኤሌክትሮኒክስና በኮንስትራክሽ ዘርፎች በተሰማሩ ነጋዴዎች ላይ ባካሄደው የተጠና ኦፕሬሽን 35 ተጠርጣሪዎች ያለደረሰኝ ሽያጭ ሲፈፅሙ እጅ ከፍንጅ ተይዘው በህግ ቁጥጥር ስር ማዋሉ ይታወሳል፡፡
🙏2
በዛሬው እለት የተመረቀው የሸበሌ ሪዞርት በምስል:-
2
የፕላስቲክ ከረጢቶችን መጠቀም የሚከለክለው አዋጅ ተግባራዊ ሆኗል

ጥር 23 / 2018 ዓ.ም አዲስ አበባ

ለአንድ ጊዜ ብቻ ጥቅም ላይ የሚውሉ የፕላስቲክ ከረጢቶችን መጠቀም የሚከለክለው አዋጅ ከጥር 23 ጀምሮ ተግባራዊ ተደርጓል አለ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን፡፡

አዋጅ ለማስፈጸም የተሰጠው የ6 ወራት ቀነ ገደብ ከዛሬ ጥር 23 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በመጠናቀቁ ነው ቅጣቱ ተግባራዊ መሆን የጀመረው፡፡

የፕላስቲክ ውጤቶች በአፈር ውስጥ ሳይበሰብሱ ከ100 ዓመት በላይ የሚቆይ በመሆኑ የውሃ አካላት መበከል፣ ብዝሃ ሕይወት መጎዳት፣ በምርትና ምርታማነት ላይ ተፅዕኖ ከማድረስ በላይ የሰውንና አካባቢ ጤናን በመበከል ከፍተኛ ጉዳት ያደርሳሉ፡፡

በዚህም ዜጎች በንጽሕ እና ጤናማ አካባቢ የመኖር መብትን ለማረጋገጥ የዜጎችን ጤንነት ከካንሰርና ሌሎች በሽታዎች በመከላከል ዘላቂ የአካባቢ አያያዝ ሥርዓትን ለማስፈን መንግሥት ለአንድ ጊዜ ብቻ ጥቅም ላይ የሚውሉ የፕላስቲክ ከረጢቶችን ማምረት፣ ወደ ሃገር ውስጥ ማስገባት፣ ማከማቸት፣ መሸጥና መጠቀም በደረቅ ቆሻሻ አያያዝ እና አወጋገድ አዋጅ 1383/2017 የተከለከለ መሆኑን ደንግጓል፡፡

የፕላስቲክ ከረጢቶችን ከጥር 23 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ የተጠቀመ ወይም ለመጠቀም ይዞ የተገኘ ማንኛውም ግለሰብ ከ2 ሺህ ብር የማያንስ ከ5 ሺህ ብር የማይበልጥ የገንዘብ ቅጣት እንደሚጣልበት ተመላክቷል፡፡

ሁሉም ዜጋ ሕጉን በማክበር ራሱን እና አካባቢውን ከፕላስቲክ ብክለት በመከላከል እንዲሁም ከሕግ ተጠያቂነት እራሱን በመጠበቅ የዜግነት ኃላፊነቱን እንዲወጣ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ጥሪ አቅርቧል፡
5
#ዛሬ_እሁድ_ምሽት 1:30 ይጠብቁን!! 👇👇👇

#በፋና_ሚዲያ_ኮርፖሬሽን ፋና ቲቪ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ #በገቢ_አዲስ #በምሽት_የመኪና ላይ በካሜራ የተደገፈ  የደረሰኝ ቁጥጥር እና ተያያዥ ጉዳዮች የተሰናዳ ፕሮግራም ይዞላችሁ ይቀርባል።
#በፋና ሚዲያ ኮርፓሬሽን  ዛሬ እሁድ ምሽት 1:30 ጀምሮ  በፋና ቲቪ ይከታተሉ ፣ ይጠብቁን  !!

#ገቢ_ለአዲስ!  ፕሮግራም ላይ ዛሬ እሁድ ጥር  24  / 2018 ዓ.ም  ምሽት ከ1:30 ጀምሮ  በልዩ መሰናዶ #በፋና_ቲቪ  ይጠብቁን !ይከታተሉ !
#ገቢ_ለአዲስ በፋና ሚዲያ  ኮርፖሬሽን #በፋና_ቴሌቪዥን#FMC ዛሬ እሁድ በ24 /2018 ዓ.ም  ምሽት ከ1:30 ጀምሮ ይተላለፋል ፕሮግራሙን ከወዲሁ ይከታተሉት ዘንድ ተጋብዘዋል !!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የኮሙንኬሽን ዳይሬክቶሬት !!

ወቅታዊ_እና_የተሟሉ_መረጃዎችን_ለማግኘት፡-
#በድረ-ገጽ_እና_ማኅበራዊ_ሚዲያ፡-
ድረ ገጽ፦ www.aarevenuesbureau.gov.et
   ቴሌግራም፦ https://t.me/aarevenues
   ቴሌግራምhttps://t.me/aacarb/1
   ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/share/p/17D365kZtf/
   ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/@addisababarevenuesbureau
   ቲክቶክ፡- tiktok.com/@addis.ababa.revenue
   ኢንስታግራም:- https://www.instagram.com/stories/addisababarevenue
   Linkedin:- https://www.linkedin.com/.../addis-ababa-revenues-bureau...
   imo https://www.imo.com.addis ababa revenues bureau
#በቴሌቪዥን_ፕሮግራሞቻችን፡-
ፋና ቴሌቪዥን እሁድ ማታ ከ1፡30 ዜና በኋላ፣
ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን /ኢ.ቢ.ሲ/ ሰኞ ማታ ከ3፡00 ዜና በኋላ፣
#በሬድዮ_ፕሮግራሞቻችን፡-
አዲስ ሚዲያ ኤፍ ኤም ሬድዮ 96.3 ማክሰኞ ከ5:00 - 6:00፣
#በወርሃዊ_ጋዜጣችን_እና_ነጻ_ጥሪ_አገልግሎት፡-
ገቢያችን ህልውናችን ወርሃዊ ጋዜጣ እንዲሁም  በነጻ ጥሪ አገልግሎታችን፡- 7075 ላይ በነፃ በመደወል መረጃዎችን መጠየቅ ይችላሉ።
3
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ነገ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ይሰጣሉ ።

ጥር 25 / 2018 ዓ.ም አዲስ አበባ

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት በ5ኛ ዓመት የስራ ዘመኑ10ኛ መደበኛ ስብሰባውን ነገ ያካሂዳል።

ም/ቤቱ በነገ ስብሰባው የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በፌዴራል መንግስት የ2018 በጀት ዓመት የ6 ወራት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ከምክር ቤት አባላት ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች የሚሰጡትን ምላሽና ማብራሪያ የሚያዳምጥ ይሆናል።
6