የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ Addis Ababa Revenues Bureau
6.28K subscribers
11.2K photos
156 videos
9 files
1.04K links
Download Telegram
በአዲስ አበባ ቴወድሮስ አደባባይ ጋር የተገነባው የድል ፕላዛ እና ቁርጡሚ የወንዝ ዳርቻ ልማት በውስጡ ያካተታቸው:-

👉 21 ሺህ 906 ካሬ ሜትር የወለል ስፋት ያለው ፕላዛ፣
👉 በአንድ ጊዜ 500 መኪናዎችን ማቆም የሚችሉ ባለ ሦስት ወለል የመሬት ውስጥ ወለሎችን (Basements parking) መኪና ማቆሚያ
👉 ዘመናዊ የፓርኪንግ ማኔጅመንት ሲስተም፣
👉 የኤሌክትሪክ መኪና ቻርጅ ማድረጊያ ጣቢያ እና የእሳት አደጋ መከላከያ ዘዴ የተገጠመለት
👉 7 ሄክታር መሬት የሚሸፍን ውብ የአረንጓዴ ስፍራ፣
👉 ምቹ የእግረኛ መንገዶች፣ ዘመናዊና ባህላዊ የስጦታ ዕቃ መሸጫዎች፣
👉 ሬስቶራንቶች፣ ካፌዎች እና ቢሮዎች
👉 2.2 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የቁርጥሜ የወንዝ ዳርቻ ልማት ፤
👉 የተለያዩ የሕዝብ አገልግሎት መስጫዎች፣
👉 የሕፃናት የአዋቂዎች ስፖርት ማዘውተሪያዎች
👉 የህፃናት መጫወቻ
👉 የስፓርት ሜዳ
👉 ⁠5 አንፊ ትያትር
👉 የህናት ማቆያ( daycares)
👉 የህዝብ መፀዳጃ ቤቶች
👉 ወደ ጐላ ሚካኤል የሚሻገር ድልድይ ተገንብቷል::
5
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የነበራቸውን የስራ ጉብኝት አጠናቀው ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል።

#PMOEthiopia
4
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ጉብኝት ተመልሰው በቀጥታ ወደ አርባምንጭ አቅንተዋል።

በአርባ ምንጭ ዙሪያ እና በመላው ጋሞ ዞን በደረሰው አደጋ ሕይወታቸውን ላጡ እና ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ሐዘናቸውን ለመግለጽ እና የሚከናወኑ የድጋፍ ስራዎችን ይገመግማሉ።

‎ለቀናት የዘለቀው ከባድ ዝናብን ተከትሎ በአካባቢው የተከሰተው ጎርፍ፤ የመሬት መንሸራተት አደጋ የዜጎቻችንን ህይወት ቀጥፏል፣ በንብረት ላይ ጉዳት አድርሷል።

ከመጠን በላይ የሞላው የኩልፎ ወንዝም መንደሮችን፣ ቤቶችን፣ የእርሻ ስፍራዎችን፣ የአካባቢ መሠረተ ልማትን አውድሟል።

ማኅበረሰቡ በከባድ ሀዘን በሚገኝበት በዚህ አስቸጋሪ ወቅት የነፍስ አድን ስራዎችን አጠናክሮ በመቀጠል ከተጎጂ ቤተሰቦች ጎን መቆም ይገባናል።

#PMOEthiopia
4
ዛሬ ማለዳ 2ኛው ከተማ አቀፍ የአዲስ አበባ ፖሊስ ስፖርት ውድድርና ፌስቲቫል በድምቀት ተጀምሯል።

"ተልዕኮን በጀግንነት፣ ስፖርትን በውጤት" በሚል መሪ ቃል የሚካሄደው 2ኛው ከተማ አቀፍ የአዲስ አበባ ፖሊስ ስፖርት ውድድርና ፌስቲቫል ዛሬ በአበበ ቢቂላ ስታድየም በድምቀት ተጀምሯል። በስድስት የስፖርት አይነቶች የሚካሄደው ይህ ውድድር፣ ከዛሬ ጀምሮ ለሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት በከተማዋ በሚገኙ የተለያዩ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች የሚቀጥል ይሆናል ።
የፖሊስ ሰራዊት ከሰላም ጥበቃ ተልዕኮው ጎን ለጎን፣ የሀገርን ስም የሚያስጠሩና ሰንደቅ ዓላማን በዓለም አቀፍ መድረኮች ከፍ የሚያደርጉ ዝነኛ ስፖርተኞችን በማፍራት ረገድ የማይተካ ሚና እያበረከተ ይገኛል፣ ይህ ተሳትፎ በቀጣይም ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ !
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
2