በቢሮው የቴክኖሎጂ አጠቃቀም በማጎልበት በአገልግሎት አሰጣጥ የሚስተዋሉ ችግሮች ለመቅረፍ በሚደረጉ ጥረቶች የመጡ ለውጦች ቀጣይነት ማረጋገጥ እንደሚገባ ያነጋገርናቸው ግብር ከፋዮች ገለፁ ።

ጥር 28 / 2018 ዓ.ም : አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ
የቢሮ አገልግሎት አሰጣጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ መምጣቱን በአዲስ አበባ ከፍተኛ ግብር ከፋዮች እና በአዲስ አበባ ቁጥር 2 መካከለኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች ሲገለገሉ ያገኘናቸው ግብር ከፋዮች ገለጹ።
ቢሮው በቅርቡ የጀመራቸው የሪፎርም ስራዎች እና የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ለለውጡ ዋነኛ ምክንያቶች መሆናቸውን አስተያየት ሰጪዎቹ ጠቁመዋል።
በከተማዋ በከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ተገኝተን ያነጋገርናቸው አቶ ግርሞ አስምሮም እንደገለጹት ቀደም ሲል በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ይስተዋሉ የነበሩ ረጅም ወረፋዎችና የእንግልት ሁኔታዎች አሁን ላይ በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሰዋል ብለዋል ።
አያይዘውም የዲጂታል አገልግሎት መስፋፋት ግብር ከፋዮች ቤታቸው ወይም ቢሯቸው ሆነው በኦንላይን (Online) ሪፖርት ማድረጋቸው ጊዜያቸውን እንደቆጠበላቸው ገልጸዋል።
ወ/ሪት ምህረት ማሩ በበኩላቸው የባለሙያዎች አቀባበል በቢሮው የሚገኙ ሰራተኞች ለደንበኞች የሚሰጡት ምላሽ እና የሚያሳዩት ትብብር የሚበረታታ መሆኑን ተናግረዋል።
በአዲስ አበባ ቁጥር 2 ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አገልግሎቱን ሲጠቀሙ ያገኘናቸው አቶ አለሙ ገብሩ ስለ ግብር አሰላሰል እና ስለ አዳዲስ መመሪያዎች የሚሰጠው ገለጻ ከጥርጣሬ ነጻ እንድንሆን አድርጎናል ብለዋል።
ከአስተያየት ሰጪዎቹ መካከል አቶ ዘካሪያስ ታደሰ የተባሉ የንግድ ስራ ባለቤት ሲናገሩ ቀደም ሲል ግብር ለመክፈል ቀናትን ይፈጅብን ነበር፤ አሁን ግን በቴክኖሎጂ የታገዘ አሰራር በመዘርጋቱ በደቂቃዎች ውስጥ ስራችንን ጨርሰን እየወጣን ነው ብለዋል።
ቢሮው በበኩሉ የአገልግሎት አሰጣጡን ይበልጥ ለማዘመን እና በየደረጃው የሚታዩ የአሰራር ጉድለቶችን ለመቅረፍ ከግብር ከፋዩ የሚመጡ ጥቆማዎችንና ቅሬታዎችን በቅርበት እየተከታተለና እየፈታ መሆኑ መሆኑ ተጠቁሟል ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *