ታህሳስ 28/2018 ዓ.ም : አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ
ይህ የተገለፀው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የንግድና ገቢ ቋሚ ኮሚቴ የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮን የ6 ወር ስራ አፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ ባካሄደበት መድረክ ነው።
በመድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የንግድና ገቢ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ስንታየሁ ደስታ ቢሮው አዳዲስ አሰራሮችና አደረጃጀቶች በመዘርጋትና ቴክኖሎጂ በመጠቀም የአገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻልና ፍትሃዊ የግብር ስርዓት ለመዘርጋት ለማከናወን በቻላቸው ተግባራት ተጨባጭ ለውጦች ታይተዋል ብለዋል።
በተለይም የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ላይ ባለፉት 6 ወራት የተከናወኑ ተግባራ በከተማም ግምባር ቀደም የሚያደርጉ ናቸውም ብለዋል።
በግብር ከፋዩ የሚነሱ ቅሬታዎችን ለመፍታትም የዘረጋቸውን አሰራሮች ውጤቶች የሚያበረታታና ሊጠናከር የሚገባው ነው ሲሉ ገልፀዋል።
ይሁንና የከተማ አስተዳደሩ በበጀት ዓመቱ ለማሳካት ያቀደው የ350 ቢሊዮን ብር ዕቅድ በተሟላ ደረጃ እንዲሳካ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ርብርብ ሊያደርጉ እንደሚገባ አሳስበዋል ።
የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ሃላፊ አቶ ቢኒያም ምክሩ በቢሮ የ2018 በጀት ዓመት የ6 ወር ዕቅድ አፈፃፀም ከገቢ አሰባሰብ ፣ በተዘረጉ አሰራሮችና አደረጃጀቶች ፣በቴክኖሎጂ ልማት፣ በህግ ማስከበር እንዲሁም ከአገልግሎት አሰጣጥ አኳያ የተሰሩ ስራዎች እና የተገኙ ውጤቶች ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥተዋል ።
ፍትሀዊ የታክስ ስርዓት በማስፈን የሚጠበቀውን ገቢ ለመሰብሰብ ይቻል ዘንድ የግብር ከፋዮች ምዝገባ ፣ የቤት ለቤት ፣ የመጋዘን እና የመኪና ላይ የደረሰኝ ቁጥጥር እየተደረገ መሆኑን ገልፀው ድንገተኛ የኦፕሬሽን ስራዎችን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስገንዝበዋል ።
የግበር ከፋዩን የህግ ተገዥነት ለማሳደግ የሚያስችሉ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ጠቁመው ።
በመጨረሻም ከግብር ከፋዩ ቅሬታ በመነሳት አገልግሎት አሰጣጡን ከማዘመንና ፈጣንና ተደራሽ ከማድረግ አኳያ የተጠያቂነት አሰሮችን በመዘርጋት እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል ።
በመድረኩ ከቋሚ ምክር ቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች የቢሮው ሀላፊዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል ።
