የካቲት 04 ቀን 2018 ዓ.ም፣ አዲስ አበባ፣ ገቢዎች ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት ፍትሃዊ የግብር አሰባሰብ ስርዓትን ለማጎልበት፣ የገቢ መሰረት ለማስፋትና የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮች ለመቅረፍ የአሰራር፣ የአደረጃጀት፣ የቴክኖሎጂ ልማትና የሰው ሀብት ልማት የሪፎርም ተግባራት ለይቶ ወደ ተግባር ማሸጋገሩ ይታወቃል፡፡
በቢሮው በጥናት ተለይተው ወደ ተግባር የተሸጋገሩ የሪፎርም ተግባራት ለከተማዋ ሁለንተናዊ ልማት የሚውል ገቢ በፍትሃዊነት ለመሰብሰብ እንዲሁም በአገልግሎት አሰጣጥ የሚስተዋሉ ችግሮች ለመቅረፍ የሚያስችል ተቋማዊ አቅም ለመፍጠር ታቅደው ወደ ተግባር የተሸጋገሩ ናቸው፡፡
በዛሬው ዕለትም የቢሮው ከፍተኛ አመራሮች በተቋሙ ወደ ተግባር የተሸጋገሩ የሪፎርም ስራዎች በስሩ ከሚገኙ 17 ቅርንጫፎች መካከል በከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ፅ/ቤት በአካል በመገኘት በምን አግባብ እየተተገበሩ መሆናቸውን ምልከታ አካሂደዋል፡፡
በምልከታው የቢሮው ኃላፊ አቶ ቢኒያም ምክሩ በቅርንጫፍ ፅ/ቤቱ በቢሮው ወደ ተግባር የተሸጋገሩ የአሰራር፣ የአደረጃጀት፣ የቴክኖሎጂ ልማትና የሰው ሀብት ልማት ሪፎርም ተግባራት ተስፋ ሰጪ ውጤቶች መመልከት ችለናል ብለዋል፡፡
በቢሮው የሞደርናይዜሽን ዘርፍ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ መሀመድ አብዱራማን በበኩላቸው በቢሮው እየተከናወኑ የሚገኙ የሪፎርም ተግባራት በቅርንጫፍ ፅ/ቤቱ ውጤታማ በሆነ መልኩ እየተተገበሩ መሆናቸውን በምልከታችን አረጋግጠናል ብለዋል፡፡
አክለውም ቢሮው በሁሉም ቅርንጫፎች በግብር ከፋዮች ከፍትሃዊ የግብር አሰባሰብ እንዲሁም ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ የሚነሱ ችግሮች ለመቅረፍ የአሰራር፣ የአደረጃጀት የቴክኖሎጂ ልማትና የሰው ኃይል ግንባታ ሪፎርሞች ወደ ተግባር አሸጋግሯል ሲሉ ገልጸዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት በቅርንጫፍ ፅ/ቤቱ ቫት የሚያሳውቁ ግብር ከፋዮች መቶ ፐርሰንት ኦንላይን በማሳወቅ እንዲሁም ከኢ-ፋይሊንግና ከኢ-ፔይመንት፣ ከታክስ ዕዳ ክትትልና አስተዳደር፣ ከታክስ ውሳኔ ስርጭት፣ ከክሊራንስና ከመሳሰሉ አገልግሎቶች ጋር በተያያዘ ወደ ተግባር የተሸጋገሩ የቴክኖሎጂ ውጤቶች አበረታች ለውጦች የተመዘገበባቸው መሆናቸውንም ተናግረዋል፡፡
ቢሮው በ2018 በጀት ዓመት በስሩ ከሚገኙ 17 ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች መካከል በሪፎርም ስራዎች ትግበራ የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ፅ/ቤቱን ጨምሮ 3 መካከለኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶችን ሞደል ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች በማድረግ ወደ ሁሉም ቅርንጫፎች ተሞክሮዎችን ለማስፋት አቅዶ እየሰራ እንደሆነም ጠቁመዋል፡፡
የቢሮው አመራሮች በከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ፅ/ቤት በመገኘት ቢሮው ለከተማዋ ልማት የሚውል ገቢን በፍትሃዊነት ለመሰብሰብ አቅዶ ወደ ተግባር ያሸጋገራቸው የሪፎርምና የተቋም ግንባታ ስራዎች አተገባበር ምልከታ አካሄዱ፡፡
