የኢኮኖሚ ነፃነቷን በማረጋገጥ የበለፀገች ሀገር መገንባት የዚህ ትውልድ ተቀዳሚ አጀንዳ ሊሆን እንደሚገባ ተጠቆመ፡፡

የካቲት 09/2018 ዓ.ም
የቢሮው አመራሮችና ሰራተኞች 130ኛው የአድዋ ድል ምክንያት በማድረግ ውይይት አካሄዱ፡፡
የአድዋ እሴት ለሁለንተናዊ ሃገራዊ ማንሰራራት” በሚል መሪ ሃሳብ የሚከበረውን የድል በአል አስመልክቶ የተዘጋጀ ሰነድ ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡
በውይይቱ የፅ/ቤት ኃላፊው አቶ አዳነ ሱሌ አድዋ ዘመን የማይሽረው በደማቅ የተጻፈ የድል ታሪክ፣ ጀግኖች አባቶቻችን ድንበር ተሻጋሪና ለጥቁር ህዝቦች ሁሉ የነጻነት ቀንዲል የሆኑበት፣ ለእኛ ኢትዮጲያውን ደግሞ የታሪካችንና የነጻነታችን ኩራት መገለጫና በአለም ሉአላዊነታችንን ያስመሰከርንበት ድላችን ነው ብለዋል፡፡
በመሆኑም የተረከብናትን ሉአላዊት ሃገር አንድነቷ የተጠበቀና የጠነከረ ምቹ የፖለቲካ ምህዳር የሰፈነባት መሆኗን በመረዳት ኢኮኖሚያዊ ብልጽግናዋን በማረጋገጥ ከበለጸጉት ሃገራት ተርታ ማሰለፍ ይገባል ብለዋል፡፡
የዴሞክራሲ ስርዓት ከመገንባት አኳያም 7ኛው ሃገር አቀፍ ምርጫም ፍትሃዊ፣ዴሞክራሲያዊና ተአማኒነት ያለው እንዲሆን ሚናችንን ልንወጣ ይገባል፡፡
የገቢ ሰብሳቢ ተቋሙ አመራርና ሰራተኛ ዋነኛ ተልዕኮ በከተማችን ፍትሃዊ የገቢ አሰባሰብ ስርዓት በማረጋገጥ ለከተማችን ልማት የሚውል ገቢ በብቃት መሰብሰብ ነው ያሉት ኃላፊው ለዚህ ተልዕኮ ሁሉም ኃላፊነቱን በሚገባ ሊወጣ ይገባል ብለዋል፡፡
የውይይት ሰነዱን ያቀረቡት አቶ ሰውነት አየለ በበኩላቸው በአድዋ ድል የተገኘ አንድነት ማስቀጠል የዘመኑ ትውለድ ታላቅ አደራ ነው ካሉ በኃላ ትውልዱ ከባዳና ባንዳዎች የሚወረወሩ የሃሰት ትርክቶችን በመዋጋት ዜጎች ሰላማዊና ግልጽነትን የተላበሰ ሃገርን የሚያሻገር ዴሞክራሲያዊ ምርጫ በማድረግ የበኩላችንን አበርክቶ መወጣት ይጠበቅብናል በማለት ተናግረዋል፡፡
በመድረኩም በቀረበው የውይይት መነሻ ሰነድ ላይ በተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ከመድርክ መሪዎች ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *