ለግንዛቤዎት

የግብር ከፋዩን የሂሳብ መዝገብ የሚያዘጋጁ የሂሳብ አዋቂዎች እና የውጪ ኦዲተሮች ኃላፊነት እና ሚና

• የሂሳብ ባለሙያው የግብር ከፋዩ አመታዊ ግብር ለማሳወቅም ሆነ ለመደበኛ የኦዲት ስራ የሚያዘጋጀው የሂሳብ መዝገብ በቢሮው በተዘጋጀው የአሰራር ሰነድ ላይ የተመላከቱ ጉዳዮች በሚቀርበው የሂሳብ መዝገብ ውስጥ በአግባቡ ማካተቱን የማረጋገጥ ሀላፊነት አለበት፣ ለዚህ ስራ ያግዘው ዘንድ ከግብር ከፋዩ ሊቀበላቸው የሚገቡ ሰነዶችና መረጃዎችን ለይቶ የመጠየቅና መረጃውንና ሰነዶችን አደራጅቶ ማቅረብ ይጠበቅበታል፣

በታክስ ህጎች፣ በፋይናንስ ሪፖርት አዘገጃጀትና አቀራረብ አዋጅና ደንብ መሰረት የሪፖርት አቅራቢ ታክስ ከፋዮችን የሂሳብ መዝገብ የሚያዘጋጁ ባለሙያዎች በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት ስታንዳርዶች መሰረት የሂሳብ መዝገቦችን በጥራት የማዘጋጀትና ሪፖርት ማቅረብ ኃላፊነት፣

• በሪፖርት አቅራቢ አካል ያልሆኑ ታክስ ከፋዮችን ደግሞ በአጠቃላይ ተቀባይነት ባለው የሂሳብ አያያዝ መመሪያዎች አግባብ የሂሳብ መዝገቡን አዘጋጅተው የማቅረብ ኃላፊነት ፣

• የሪፖርት አቅራቢ አካላትን የሂሳብ ዓመቱን የፋይናንስ ሪፖርት በሚያዘጋጁበት ወቅት ከታክስ ህጎች ጋር ልዩነት ያላቸውን የሂሳብ አያያዝ ዘዴዎችን (Accounting methods) በፋይናንስ ሪፖርት ደረጃዎች (IAS-12) መሰረት ልዩነቶችን በሂሳብ መመዝገብ በመግለጫ የማሳየት ኃላፊነት፣

• የውጭ የሂሳብ ባለሙያዎች (የተፈቀደላቸው የሂሳብ አዋቂዎች ከደንበኞቻቸው ጋር ያላቸው ግንኙነት እንዲሁም በሂሳብ አዘገጃጀትና ሪፖርት አቀራረብ ጋር በተያያዘ በጋራ እና የተናጥል ኃላፊነታቸውን በግልፅ በወል የማስቀመጥ፣

• የታክስ ስርዓትን ለማዘመን ደንበኞቻቸውን በታክስ ዙሪያ ያላቸውን የግንዛቤ ክፍተቶችን በሙያቸው በማገዝ በራስ አነሳሽነት ታክስ በትክክል የማሳወቅ እና የመክፈል ባህል እንዲዳብር የሂሳብ አዋቂዎችና የውጭ ኦዲተሮች ከፍተኛና የማይተካ ሚና እንዳላቸው አውቀው በከፍተኛ የሙያ ደረጃ በመጠበቅ የህዝብ ጥቅምን የማስጠበቅ ኃላፊነት ይኖርባቸዋል፣

• የታክስ ባለስልጣኑ የግብር ከፋዩን የሂሳብ መግለጫ ኦዲት በሚያደርግበት ወቅት የሰሩትን የሂሳብ ስራ ማብራሪያ ለመስጠት ሁልጊዜ ዝግጁ መሆን፣

• ህገ ወጥ የሂሳብና ኦዶት ስራን ለመከላከል ይቻል ዘንድ የተፈቀደላቸው የሂሳብ አዋቂዎች እና ኦዲተሮች የደንበኞቻቸውን ዝርዝር ሲጠየቁ ለታክስ ባለስልጣኑ የማሳወቅ ኃላፊነት፣

• የህዝብን ጥቅም የሚጎዱ ተግባራት ላይ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ አለመሳተፍ፣ ደንበኞቻቸው በመሰል ተግባር ላ ተሳትፎ ያላቸው መሆኑን የሚያውቁ ከሆነ ህግ እንዲያከብሩ የሙያ ኃላፊነታቸውን የመወጣት፣

• የሚቀርቡ የሂሳብ መዝገቦች በታክስ ባለስልጣኑ ኦዲት በሚደረግበት ጊዜ ልዩነት እንዳያጋጥም በታክስ ህጎች እና ማዕቀፎች በጠበቀ መልኩ ማዘጋጀት፣

• የግብር ከፋዩን የሂሳብ መዝገብ የሚያዘጋጁ የሂሳብ ባለሙያዎችና ኦዲተሮች የሚያዘጋጁት የሂሳብ መዝገብ የጎላ ጥራት ጉድለት ከተገኘ ተጠያቂ የሚሆኑነት አሰራር እንደተዘረጋ መገንዘብ፣

• የደረጃ ‹‹ሀ›› ግብር ከፋዮች የንግድ ስራ ገቢ እና የኪራይ ገቢ ግብር የመክፈል ኃላፊነት የተጣለባቸው ግብር ከፋዮች ጥሬ ገንዘብን መሰረት ያላደረገ (accrual base) የሂሳብ አያያዝ ዘዴ መሰረት የሂሳብ መዝገባቸውን ማዘጋጀት ይኖርባቸዋል፡፡ በዚህ የሂሳብ አያያዝ ጥሬ ገንዘብ ስራ ላይ ባይውልም ( ክፍያ ባይፈፀምም እንዲሁም ገቢ ባይሰበሰብም) ስራዎቹ በጥሬ ገንዘብ እንደተከናወኑ የሚቆጥር የሂሳብ አያያዝ ሲሆን ለተከፋይና ተሰብሳቢ ሂሳቦች ዕውቅና ይሰጣል፡፡ በዚህም መሰረት ክፍያ ሳይፈፀም ለሚገዛ ዕቃ ወጪ ተብሎ የሚያዝ ሲሆን በዱቤ ለሚሸጥ ዕቃ እንደ ገቢ እንዲያዝ የሚያደርግ የሂሳብ ዘዴ ነው፡፡

• በታክስ ህጎች ፣ በፋይናንስ ሪፖርት አዘጋጃጀትና አቀራረብ አዋጅና ደንብ መሰረት ሪፖርት አቅራቢ ታክስ ከፋዮች እና የሂሳብ መዝገቡን የሚያዘጋጁ ባለሙያዎች በዓለም አቀፉ የፋይናንስ ስታንዳርዶች መሰረት የሂሳብ መዝገቦችን በጥራ ማዘጋጀትና ሪፖርት ማቅረብ ኃላፊነት፣

• የንግድ ስራ እና የኪራይ ገቢ ያላቸው ግብር ከፋዮች የተለያየ መዝገብና የሂሳብ መግለጫዎች የማዘጋጀት፣

• የሚቀርቡት የፋይናንስ ሪፖርቶች የሐብትና ዕዳ፣ የትርፍና ኪሳራ፣ የሐብት ለውጥ እና የጥሬ ገንዘብ ፍሰት የሂሳብ መግለጫዎች እንዲሁም የእነዚህ የሂሳብ መግለጫዎች ማብራሪያዎችና ማስታወሻዎችን የማካተት፣

• የኦዲት ስራው በዋናው መስሪያ ቤት በተደራጀው የታክስ ውሳኔ ጥራት የሚያረጋግጥ የስራ ክፍል በድጋሚ ኦዲት እንደሚደረግ በመረዳት የኦዲት ስራው በአግባቡ ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ ብልሹ አሰራር ላይ ባለመሳተፍ እና ባለመተባበር በታማኝነት ኃላፊነትን መወጣት ከግብር ከፋዩ ይጠበቃል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *