ቢሮው በ2018 በጀት አመት የሌብነትና ብልሹ አሰራር ፣ የመልካም አስተዳደር፣ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮች በመቅረፍና የተጠያቂነት አሰራር በማጠናከር የታክስ ፍትሃዊነት ለማረጋገጥ በትኩረት እንደሚሰራ ተገለፀ፡፡

ነሐሴ 10 / 2017 ዓ.ም አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በዋና መስሪያ ቤቱ ፣ በ17ቱ ቅርንጫፎችና በወረዳ ካሉ ከ 7ሺህ በላይ ከሆኑ አመራሮችና ሰራተኞችጋር በመልካም አስተዳደር፣ በአግልግሎት አሰጣጥና በሌብነትና ብልሹ አሰራር ዙሪያ ውይይት አካሂዷ፡፡

በውይይቱ የቪዲዮ ገለፃ ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ሀላፊ አቶ ቢንያም ምክሩ በ2018 በጀት ዓመት ቢሮው በአገልግሎት አሰጣጥ መሰረታዊ ለውጥ በማምጣት የግብር ከፋዮች እርካታ ለማሻሻል በትኩረት ይሰራል ብለዋል፡፡

በተቋሙ የሚታዩ የሌብነት ፣ የብልሹ አሰራር ፣ የመልካም አስተዳደር እና የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮች ፍትሀዊ የታክስ አሰባሰብ በተሟላ ደረጃ እንዳይዘረጋ እንቅፋት የሚፈጥሩ መሆናቸው ያነሱት ኃላፊው ችግሮቹን ለመቅረፍ ሁሉም የተቋሙ አመራርና ባለሙያ ሚናውን በአግባቡ ሊወጣ ይገባል ብለዋል፡፡

የተጠያቂነት ስርዓት ከማጠናከር አኳያም ከተመደቡበት የታክስ ሴንተር ውጪ ቫት ለግብር ከፋዮች በቋሚነት ሲያሳውቁ የነበሩ 115 ባለሙያዎችን እንዲሁም በየቅርንጫፉ ግብር ከፋዮች የሚጠበቅባቸው ግብር ሳይከፍሉ ክሊራንስ የሰጡ 16 ባለሙያዎች ተጠያቂ መደረጋቸውንም አንስተዋል፡፡

ቢሮው በበጀት ዓመቱ የአገልግሎት አሰጣጥና የመልካም አስተዳደር እንዲሁም የሌብነትና ብልሹ አሰራሮች በዘላቂነት ለመቅረፍ የሚያግዙ አሰራሮችና አደረጃጀቶች በጥናት በመለየት ወደ ተግባር ማሸጋገሩን በመግለፅ አገልግሎቶች በቴክኖሎጂ እንዲደገፉ በውስጥ አቅምና ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት የለሙ ቴክኖሎጂዎች ወደ ተግባር እየተሸጋገሩ ናቸው ብለዋል፡፡

በ2018 በጀት ዓመት የግብር ከፋዩን እርካታ ለማሻሻል በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የገለፁት አቶ ቢኒያም የተጠያቂነት አሰራርን በማጠናከር የመልካም አስተዳደር፣ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮች በተሟላ ደረጃ ለመቅረፍ ይሰራል ብለዋል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ በማዕከልም ሆነ በቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች በሌብነትና ብልሹ ድርጊት ውስጥ የገቡ ብቻም ሳይሆን ለግብር ከፋዩ ተገቢውን ክብር የማሰጡ፣ ስራዎችን በጥናት በተለዩ ስታንዳርዶች የማይፈፅሙ፣ ለግብር ከፋዮች ተገቢውን አገልግሎት የማይሰጡ ጭምር ተጠያቂ ይሆናሉ ሲሉም ተናግረዋል፡፡

በመጨረሻም በማዕከል ቢሮና በ17ቱ ቅርንጫፎች ፅ/ቤቶች በመድረኩ ተሳታፊዎች በቀረበው ገለፃ መነሻነት ሰፊ ውይይት የደረጉ ሲሆን ከሌብንትና ብልሹ ድርጊቶች ጋር በተያያዘ በጥቂት ባለሙያዎች የተቋሙ ስም መጠልሸት ስለሌለበት የተጠያቂነት አሰራሩ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባልም ብለዋል፡፡

ከመልካም አስተዳደርና አገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተመለከተም ለግብር ከፋዮች ተገቢውን አገልግሎት በመስጠት እንዲሁም የተዘረጉ አሰራሮች በአግባቡ በመተግበር የሌብነትና ብልሹ አሰራር ለመቅረፍ ኃላፊነታችንን እንወጣለን ሲሉ ተናግረዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *