በመርካቶ በቴክኖሎጂ የታገዘ የቁጥጥር ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገለፀ ።

ነሐሴ 13 / 2017 ዓ / ም የአዲስ አበባ፣ ገቢዎች ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የቁጥጥር ስራው በቴክኖሎጂ እንዲታገዝ በማድረግ ወደ ተግባር ማሸጋገሩ ይታወቃል ።

በመሆኑም የኮሙንኬሽን የዝግጅት ክፍላችን በመርካቶ አካባቢ እየተደረገ ያለውን ቁጥጥር እየቃኘ መረጃ ማድረሱን አጠናክሮ ቀጥሎበታል ።

ቢሮው ወደ ተግባር ባሸጋገረው በቴክኖሎጂ የታገዘ የቁጥጥር ስርዓት ላይ ያለውን ሂደት በተመለከተ የዝግጅት ክፍላችን የቁጥጥር ሰራተኞች ወደ መስክ ከመላካቸው በፊት ዘወትር ጠዋት ጠዋት የስምሪትና የስራ ውሎ ውይይት መድረክ ይካሄዳል።

የዝግጅት ክፍላችንም በጠዋት በመርካቶ ተገኝቶታ የመርካቶ ቁጥር 2 የህግ ተገዢነት ዘርፍ ምክትል ስራ አስኪያጅ ኮማንደር ደራራ ጫላ የመሩትን መድረክ ተከታትሏል ።

የህግ ማስከበር ስራ ቁርጠኝነትን ፣ ታማኝነትንና አገልጋይነትን ይጠይቃል ያሉት ኮማንደር ደራራ በይበልጥም ቅንጅታዊ ስራንና ለንግዱ ማህበረሰብ ግብር ከፋይ ፍቅርና አክብሮትን በመስጠት ሁሌ መሥራት ይኖርብናል ብለዋል ።

በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመጠቀም በመርካቶ የተጀመረው የቁጥጥር ስምሪት 5 ቀናትን ቢያስቆጡሩም አመርቂና አበረታች ውጤቶች እየተገኙበት እንደሆነ በቀን ውሎአቸው ከስምሪት በፊት በሚያደርጉት ውይይት ላይ ተነስቷል ።

ከበፊቱ ቁጥጥር እጅግ ይለያል ያሉት ኮማንደር ደራራ ጫላ ከንግዱ ማህበረሰብ ( ግብር ከፋዩ ) የሚመጡልን አስተያየቶች በግልፅነት ግብር ሰብሳቢው ተቋምና እኛ ነጋዴዎች በአሰራር ተገናኝተናል ተጠናክሮ ይቀጥል የሚል እንደሆነ አብራርተዋል ።

በመርካቶ ቁጥር 2 ፣ 6 ወረዳዎችን ያካተተ 18 ቡድኖች እንዳሉና በሚመደቡበት ቡለክ የስራ ስምሪት ማን ምን፣ እንዴት ፣ ለምን እንደሚሰሩ አቅጣጫ ተሰጥቷቸው ወደ ቁጥጥር እንደሚሄዱና የውሎ ስራቸውም ተጠያቂነትንና ውጤትን መሠረት ባደረገ መልኩ በየቀኑ እንደሚገመገምና አቅጣጫ እንደሚሰጥ ከመድረኩ መረዳት ችለናል ።

የቁጥጥር ሰራተኞች በበኩላቸው የተቋሙ መለያ ዩኒፎርሙ ለብሰው ፣ ባርኮድ ያለው መታወቂያ ይዘው መንቀሳቀሳቸው ለስራው ስኬትና በግብር ከፋዩ የንግዱ ማህበረሰብ ጥሩ አቀባበልና አክብሮት እያገኙ መሆናቸውን ገልፀዋል ።

የበፊቶቹ ገቢ ሳይሆን ከገቢ ነው የመጣነው በማለት በማዋከብ ይበዘብዙን ነበር ያሉት አቶ ትዕዛዙ ቢሮው ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ተጠቅሞ አዳዲስ አሰራሮችን ወደ ተግባር ማሸጋገሩ ገቢው በወቅቱና በአግባቡ እንዲሰበሰብ ያስችላል ሲሉ ገልፀውልናል ።

የቁጥጥር ሰራተኞች በየቀኑ ጠዋት ጠዋት ወደ ስምሪት ከመሄዳቸው በፊት የሚያደርጉት ውይይትና የቀጣይ ስራ አቅጣጫ የቁጥጥር ስራው በተገቢ ሁኔታ ለመምራትና የሚጠበቀውን ውጤት ለማምጣት የሚያስችል እንደሆነ ተመላክቷል ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *