ገቢ በብቃት የመሰብሰብ አቅም በማሳደግ የከተማዋ የወጪ ፍላጎት ለማሟላት የሚያስችል ግብር ከፋዮች የህግ ተገዥነት ደረጃ ማጎልበት እንደሚገባ ተገለፀ ።

ነሀሴ 15 / 2017 ዓ.ም : አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ

በአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የታክስ ዘርፍ እስከ ነሀሴ አጋማሽ የተከናወኑ የህግ ማስከበር ስራዎችን የከተማዋን ፍላጎት ለማሟላት የሚያስችል እና የህግ ተገዥነት አቅም ማሳደግ ያስቻለ መሆኑን ገምግሟል ።

የውይይቱን መድረክ የመሩት በቢሮው የህግ ተገዥነት ምክትል ቢሮ ኋላፊ አቶ ሚኪያስ ሙሉጌታ የመረጃ ማጥራት ፣ የቁጥጥር ስራ ሂደት በትንተና የተደገፈ መሆኑ ፣ የሚወጡ የኢንቨስትጌሽን ውሳኔዎች ሽፋን ጥራቱን የጠበቁ መሆናቸው እንዲሁም ከተቋሙ የሚወርዱ አሰራሮችን በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት መተግበራቸውን በአንክሮ መመልከት እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል ።

አያያዝወም የንግድ ቁጥጥር ማጠናከር ፣ ፣ የቅጣት ውሳኔ አሰጣጥ መከታተል ፣ ደረሰኝ የሌላቸው እንዲጠቀሙ የማድረግ ፣ የሽያጭ መመዝገቢያ ማሽን እንዲጠቀሙ የማስቻል እንዲሁም ተቆጣጣሪዎች በአግባቡ የእኛን ግብር ከፋዮች እየተቆጣጠሩ መሆኑን መከታተል እና ሁሉም ቅርንጫፍ በወረደው ዕቅድ መሰረት በወጥነት ሊያከናውኑ እንደሚገባ አመላክተዋል ።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ወደ ቫት መግባት እየተገባቸው ያልገቡትን እንዲገቡ የማድረግ ፣ ደረሰኝ የሌላቸው እንዲያሳትሙ ማድረግ ፣ የንግድ ፍቃድ የሌላቸው እንዲያወጡ ፣ እንዲሁም በስፔሻላይዤሽን የሚታዩ ግብር ከፋዮችን ተከታትሎ ወደ ህግ ተገዥነት የማምጣት ስራው ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው ተመላክቷል ።

የግብር ከፋዩን የታክስ ዕውቀት በማሳደግ የህግ ተገዥነቱን ደረጃ ለማሳደግ የስልጠና መድረኮችን የማመቻቸት ፣ የተለያዩ በራሪ ፅሁፎችን አዘጋጅቶ የማሰራጨት እና የማለዳ ገፅ ለገፅ ትምህርት አሰጣጥን ሁሉም ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ማጠናከር እንደሚገባ በውይይቱ ተጠቁሟል ።

የኢንቨስትጌሽንና የቁጥጥር ስራዎች የትንተና ስራ በመስራት በመረጃ መደገፍ በአግባቡ መመርመር ፣ በሞል ውስጥ ቫት መግባት ያለባቸውን ነጋዴዎች ማስገባት ፣ የህንፃ ኪራይ ገቢ በአግባቡ ለቢሮው መግባቱን የመለየት ፣ የመኪና ለይ ቁጥጥርን ማጠናከር ፣ የመጋዘን ምዝገባ ቁጥጥርን የማጠናከር ፣ የበዓል ገበያን በልዩ ትኩረት መስራት ፣ እንዲሁም የግግድ ቤቶች የገበያ ዋጋ ጥናት መጠናከር እንዲሁም የ3ኛ ወገን መረጃን ማጥራት እንደሚገባ አቶ ሚኪያስ የቀጣይ አቅጣጫ አስቀምጠዋል ።

በአጠቃላይ በወሩ ከሚሰሩ ስራዎች አኳያ መልካም ቢሆንም ከከተማችን ገቢ የመሰብሰብ እና ፍላጎት አኳያ ሊሻሻል እንደሚገባ አቶ ሚኪያስ አሳስበዋል ።

ለውይይቱ መነሻ የቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ድጋፍና ክትትል መረጃ ውጤት በዘርፋ ስር ከሚገኙ ዳይሬክቶሬች ቀርቧል ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *