ነሀሴ 30 / 2017 ዓ.ም ፡ አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ያቀረብነውን የታክስ ቅሬታ በአግባቡ በመመርመር ፍትሀዊ የሆነ የታክስ ውሳኔ ማሻሻያ አድርጎልናል ሲሉ ከዝግጅታችን ክፍል ጋር ቆይታ ያደረጉት በዚጊዛግ ሆቴልና እስፖ ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ብሩክ ተገኝ ገልፀውልናል ።
ድርጅታቸው ከዚህ በፊት እንደዚህ አይነት የታክስ ውሳኔ ደርሷቸው የማያውቅ መሆኑን የነገሩን አቶ ብሩክ ቢሮው ላቀረብነው የታክስ ቅሬታ ፍትሀዊና ፈጣን ውሳኔ ሰጥቶናል ብለዋል ።
በዚህም ከፍተኛ የታክስ ውሳኔ ተወስኖብን የነበረ ቢሆንም በቢሮው ቅሬታችን በአግባቡ ታይቶ ሊስተካከሉ የተገባቸው ጉዳዮች በሙሉ እንዲስተካከሉ በማድረግ ተገቢውና ትክክለኛ የታክስ ውሳኔ ለማግኘት ችለናል ብለዋል ።
በመሆኑም ግብር ከፋዩ ማህበረሰብ እንዲህ አይነት ውሳኔ ሲደርሳቸው ‹‹ቅሬታ ባቀርብ አይፈታልኝ›› ከማለት ይልቅ ቢሮው ባስቀመጠው የቅሬታ አቀራረብ ስርዓት መሰረት አስፈላጊውን የሰነድ ማስረጃና ማብራሪያ በማቅረብ እንዲፈታላቸው ማድረግ እንደሚችሉ ጠቁመዋል ።
በመጨረሻም በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች ቅሬታዎችን ተቀብለው የሚያዩበት እና ሰነዶችን በጥልቀት መርምሮ ውሳኔ የሚሰጥበት አግባብ የሚመሰገን ነው ብለዋል ።