ዜና ትንታኔ

=========

በገቢ አሰባሰቡ ላይ የታየው ሁሉን አቀፍ እድገትና እምርታ በቀጣይም በ2018 በጀት ዓመትም ተጠናክሮ ይቀጥላል ፡፡

ጳጉሜ 03 / 2017 ዓ / ም ፣ የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የከተማው ማህበረሰብ የመልማት ፍላጎት የመመለስ ትልቅ ኃላፊነት ወስዶ እየተጋ የሚገኝ ተቋም ነው ፡፡ በዚህም ምክንያት ቢሮው እያከናወናቸው በሚገኙ ተግባራት የተነሳ የገቢ አሰባሰቡን ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መጥቷል ፡፡ ከ2010 ጀምሮ በነበሩት የለውጥ ዓመታት የገቢ ዕድገቱ እምርታዊ ለውጥ አስመዝግቧል በ2010 ዓ.ም 33.4 ቢሊየን ብር ተሰብስቦ የነበረ ቢሆንም በ2017 በጀት ዓመት እንደ ቢሮ ከ163 ቢሊየን ብር እንደከተማ ደግሞ 233 ቢሊየን ብር ተሰብስቧል ፡፡

ይህንን የገቢ እቅድ ማሳካት የቻለው ያልተነኩ የገቢ መሰረቶችንና አቅሞችን በመለየት ገቢን አሟጦ ለመሰብሰብ ጥረት በማድረጉ፣ የታክስ ከፋዩ ሕብረተሰብ የህግ ተገዢነት ደረጃው ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱ፣ በገቢ ሰብሳቢው ተቋሙ የነበሩ የአደረጃጀት፣ የአሰራር፣ የቴክኖሎጂና የሰው ኃይል ችግሮችን ለይቶ መፍታት ተችሏል ፡፡

የገቢ አቅምን ለማሳደግ በርካታ ተግባራት ተከናውነዋል፡፡ ለአብነትም በ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያዎቹ ወራት የተጨማሪ እሴት ታክስ በየወሩ 860 ሚሊየን ብር ብቻ ይሰበሰብ ከነበረበት አዳዲስ የቫት ተመዝጋቢዎችን ወደ ስርዓቱ በማገባት በበጀት ዓመቱ የመጨረሻዎቹ ወራት የቫት ወራዊ ገቢ ወደ 2 ቢሊየን ብር በተመሳሳይ የደመወዝ ገቢ ግብር በየወሩ ከነበረበት ከ3.6 ቢሊየን ወደ በየወሩ 6.8 ቢሊየን ብር ማሳደግ ተችሏል ፡፡

ከአሰራር አንጻር መልካም አስተዳደርና የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን ለመቅረፍ፣ሌብነትና ብልሹ አሰራሮችን ለመከላከልና በታክስ ውሳኔ የቅሬታ ምንጮች ለመቅረፍ እንዲሁም ቢሮው የተሰጠው ተልእኮ ለማሳካት የሚያስችሉ 24 አሰራሮችን ዘርግቷል ፡፡

ከአደረጃጀት አኳያ ጊዜ የማይሰጡ አደረጃጀቶችን በጥናት በመለየት ወደ ተግባር እንዲገቡ ተደርጓል ፡፡ የመረጃ ቴክኖሎጂና የውሣኔዎች ጥራት ማረጋገጥ ዳይሬክቶሬት ፣ የዕዳ ክትትል አስተዳደር ዳይሬክቶሬት እና የስታንዳርዳዜሽን ሪፎርም አገልግሎት አሰጣጥ ክትትል ዳይሬክቶሬት እንዲሁም ከተደራሽነት አንጻር አዲስ አበባ ቁጥር 3 መካከለኛ ግብር ከፋች ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት በአዲስ መልክ ተቋቁሟል ፡፡

በዚህም በተቋ፣ሙ ለገቢ አሰባሰብ አጋዥ የሆኑ፣ የመልካም አስተዳደር፣ የአገልግሎት አሰጣጥ እና የሌብንትና ብልሹ አሰራር ለመቅረፍ የሚደረግ ጥረት የሚያግዙ አደረጃጀት በማጥናት ወደ ተግባር ተሸጋግረዋል ፡፡

ቢሮው የታክስ አሰባሰብ ስርዓቱ ለማዘመን ከቴክኖሎጂ አንጻር የደረጃ ሐ ግብር ከፋዮችን ግብር የሚከፍሉበት ቴክኖሎጂ E-Tax System ፣ የገቢ አሰባሰብ መረጃ መላላኪያ ቴክኖሎጂ E- revenu plan system ፣ የነጻ ስልክ መስመር 7075 ፣የእዳ ክትትል ሲስተም ፣ E-Payment & E- filing ቴክኖሎጂ፣ ፣ የደረጃ “ሐ“ ግብር ከፋዮችን ውሳኔ በአጭር በ7075 አማካይነት በSMS የጽሑፍ መልዕክት ግብር ከፋዩ ባሉት ቴሌ ብር፣ CBE ብር፣ ሞባይል ባንኪንግ ወዘተ የሚከፍሉበት ሁኔታ ተመቻችቷል።

ከዚህ በተጨማሪ የቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች አገልግሎት ከማዕከል ለመከታተል እንዲችሉ የሰርቪላንስ ካሜራ፣ ለቁጥጥር ሰራተኞች ማንነት በቀላሉ ለማወቅ እንዲቻል ባር ኮድ የተካተተበት መታወቂያ እንዲሁም በሂደት ላይ የሚገኙ Live Video & Voice Transmission እና Location Tracking ቴክኖሎጂዎችን ተግባራዊ ተደርጓል ።

ከሰው ኃይል በየደረጃው ከሚገኙ ሰራተኞች በተለይም ከታክስ ኦዲተሮች በአገልግሎት አሰጣጥና በተቋሙ ተልዕኮ ዙሪያ ውይይት በማድረግና የክህሎትና የአመለካከት ችግሮቻቸውን ለመፍታት የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች የተሰጠ ሲሆን የሠራተኛው ተነሳሽነትና የስራ ባህል ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ በመምጣቱ በተቋሙ አመራሮችና ሰራተኞች ዘንድ ማልዶ መግባትና አምሽቶ መውጣት እንዲሁም ቅዳሜ ሙሉ እና እሁድም ገብቶ በመስራት እየተለመደ መጥቷል ፡፡

ሌብነትና ብልሹ አሰራርን በዋናነት የማስተማርና አቅም የማጎልበት ስራዎች ቅድሚያ በመስጠት የተሰራ ሲሆን ለሌብነትና ብልሹ አሰራር በር የሚከፍቱ አሰራሮችን በመለየት ብልሹ አሰራር እና የሙስና ምንጮች ማክሰሚያ ሰነድ በማዘጋጀት በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች እና ፈጻሚዎች ግንዛቤ እንዲጨብጡ የማድረግ ስራ ተሰርቷል፡፡ በሌላ በኩል የተጠያቂነት ሥርዓትን ከማስፈን አኳያም 225 አመራርና ፈጻሚዎች እንደየጥፋት አይነትና ደረጃ 11 አመራሮችና ሰራተኞች ከስራ የማሰናበት፣ 41ዱ ላይ ከባድ የዲስፕሊን እርምጃ እንዲሁም 173 ቀላል የድስፕሊን እርማጃዎች ተወስዷል ፡፡

በመጨረሻም ታክስ ከፋዩ ማህበረሰብ ግብር መክፈል ክብርና ለሀገር መቆርቆር መሆኑን በመገንዘብ የሚጠበቅባቸውን ግብር በታማኝነት በወቅቱ መክፈል ፣ ከቫት ጋር በተያያዘ በየወሩ ማሳወቅ፣ በዘርፉ ሌብነትና ብልሹ አሰራሮችን ለመከላከል የበኩላቸውን ሚና መወጣት እንዲሁም አገልግሎትን በገንዘብ ባለመግዛትና ብልሹ አሰራሮችን ሲያጋጥሙ በቢሮው የነጻ የስልክ መስመር 7075 በመጠቆም ከቢሮው ጋር ተቀናጅቶ እንዲሰራ መልዕክታችንን እናስተላልፋለን ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *