መስከረም 08 / 2018 ዓ.ም አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ።
በአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት በአዲሱ ገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 1395/2017 ማሻሻያ በተደረገባቸው እና በሌሎች ጉዳዮች ዚሪያ ከተለያዩ ዘርፍ ለተውጣጡ 180 ግብር ከፋዮች የግንዛቤ ስልጠና ሰጠ ።
ግብር ከፋዮች በታማኝነት ግብራቸውን በወቅቱ እንዲከፍሉ የሚወጡ አዋጆች ፣ ህጎች ፣ መመሪያዎችና አሰራሮችን በሚገባ በመረዳት እና በመተግበር ውጤታማ ግብር ከፋይ እንዲሆኑ ለማስቻል ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቱ ፕሮግራም በማውጣት ለከፍተኛ ለግብር ከፋዮቹ ስልጠና እየሰጠ መሆኑን የቅርንጫፉ የታክስ ከፋዮች ትምህርት፣ ድጋፍና የህግ ተገዢነት የስጋት ስራ አመራር የስራ ሂደት አስተባባሪ ወይዘሮ ብርቱካን ባምላኩ ለዝግጅት ክፍላችን ገልፀዋል ።
በአዲሱ ግብር አዋጅ ዙሪያ ለግብር ከፋዮች የፌዴራል ገቢዎች ሚኒስቴር የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት የታክስ ትምህርት ዋና መሪ አቶ እንዳለልኝ አስራት በአዋጁ ዋና ዋና ጉዳዮች ዙሪያ ተሞክሮን በማጣቀስ ስልጠና ሰጥተዋል ።
በስልጠናው የተሳተፉ ግብር ከፋዮች በበኩላቸው ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቱ በሚወጡ አዋጆች፣ ደንቦች፣ ህጎች፣ መመሪያና አሰራሮች በየጊዜው ፕሮግራም አውጥተው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎች መስጠታቸውን አድንቀው፣ ይህም ግብር በምንከፍልበት ወቅት ምን ማድረግ እንደሚገባንና ከሚያጋጥሙን ችግሮች ለመውጣት ዕውቀት ያገኘንበት ነው ብለዋል ።
ስልጠናው በዋናነት የግብር ከፋዮች ደረጃዎች ፣ የሂሳብ መዝገብ አያያዝና ፋይዳ ፣ የኪራይ ገቢ ግብር ፣ ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ ግብር ፣እና ሌሎችን የዳሰሰ መሆኑ ለማወቅ ተችሏል።