ጥቅምት 5 / 2018 ዓ.ም : አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ
የቢሮው የሞደርናይዜሽንና የፅ/ቤት ዘርፍ በበጀት ዓመቱ በመጀመሪያ ሩብ ዓመት አቅዶ ያከናወናቸውን ቁልፍ እና አበይት ተግባራት አፈፃፀሙን ገምግሟል ።
የግምገማውን መድረክ የመሩት የሞደርናይዜሽን ዘርፍ ምክትል ቢሮ ሃላፊ አቶ መሀመድ አብዱረማንና የፅ/ቤት ኃላፊ አቶ አዳነ ሱሌ ናቸው።
በውይይት መድረኩም በዕቅድ አፈፃፀሙ የታዩትን ጠንካራ እና ደካማ ጎኖች ፣ የተገኙ መልካም ተሞክሮዎች እንዲሁም በቀጣይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ላይ ያመላከተ እንደሆነ አብራርተዋል ።
በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ ላይ የሚመለከታቸው የቢሮው ዳይሬክቶሬቶች ፣ የቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ስራ አስኪያጆችና የወረዳ ስራ አስተባባሪዎች እንዲሁም ስራ ሂደት አስተባባሪዎች ተሳትፈዋል ።
በግምገማዊ ውይይቱ ላይ ለተነሱ ሀሳቦች ከአመራሮቹ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶበታል ።