ጥቅምት 19 / 2018 ዓ.ም አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ።
በቢሮው የሰው ኃብት ስራ አመራር ዳይሬክቶሬት አዲስ በተሻሻለው የመንግስት ሰራተኞች አዋጅ ቁጥር 87/2017 ላይ በየደረጃው ለሚገኘው የሰው ኃብት ስራ አመራር ዳይሬክቶሬት ሰራተኞች ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እየሰጠ ነው ፡፡
በቢሮው የቢሮ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አዳነ ሱሌ በግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናው ተገኝተው እንደገለጹት ስልጠናው ለቢሮው ሰራተኞች በዕውቀት ላይ የተመሰረተ አገልግሎት ለመስጠትና የውስጥ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ከመቅረፍ አንጻር ትልቅ አስተዋጽኦ የሚያደርግ መሆኑን ገልጸዋል ፡፡
በመጨረሻም በተሰጠው ስልጣን ልክ ስራውን በዕውቀት መምራትና ለሰራተኛው ፈጣን ምላሽ መስጠት ሲገባው ሰራተኛው እንዲመላለስ፣ አገልግሎቱ እንዲበደል ባጠቃላይ የውስጥ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን እንዲፈጠሩ ማድረግ ተጠያቂነትን የሚያስከትል መሆኑን አያይዘው ገልጸዋል ፡፡
በቢሮው የሰው ኃብት ስራ አመራር ዳይሬክተር አቶ ታሪኩ ጋዲሳ የስልጠናው አላማ በተሻሻለው አዋጅ ዙሪያ ግንዛቤ በመፍጠር በሁሉም የቢሮ መዋቅር ወጥ የሆነ አገልግሎት እንዲሰጥ ለማስቻል ታስቦ መሆኑን ገልጸዋል ፡፡
አያይዘውም እንደቢሮ የታቀደው ሪፎርም ተግባራዊ ለማድረግ የዳይሬክቶሬቱ ባለሙያዎች በዕውቀት ላይ የተመሰረተ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማስቻል ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን ገልጸዋል ፡፡
በመጨረሻም በየደረጃው የሚገኙ የዳይሬክቶሬቱ ባለሙያዎች በአዋጁ በተቀመጠው አሰራር መሰረት ለሰራተኞች አገልግሎት እንዲሰጡ እንዲሁም አመራሮች አዋጁ ተግባራዊ እንዲሆን የቅርብ ክትትልና ድጋፍ እንዲያደርጉ አሳስበዋል ፡፡

 
			 
			 
			 
			