ቢሮው ፍትሃዊ የገቢ አሰባሰብን ለማስፈን የሚያደርገው ጥረት ውጤታማነት ለማላቅ የተቋማት ቅንጅት ሊጠናከር እንደሚገባ ተገለፀ ።

ጥቅምት 20 / 2018 ዓ.ም አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ

ቢሮው የበጀት አመቱን የአንደኛ ሩብ አመት የተቋማትና የባለድርሻ አካላት የቅንጅታዊ ስራዎች አፈፃፀም ግምገማ አካሄደ ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በበጀት ዐመቱ የመጀመሪያው ሩብ አመት ያቀደውን የላቀ ገቢ አሰባሰብ ለማሳካት ከባለድርሻ አካላት ጋር ቅንጅትና ትብብር በማጠናከር ያከናወናቸውን ተግባራት ዛሬ በጥልቀት በመገምገም የቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀምጧል ።

የገቢ አሰባሰቡን ውጤታማ ለማድረግ በበጀት አመቱ የሁለትዮሽ የስራ ስምምነት ውል ከተፈራረማቸው 18 ከሚሆኑ ተቋማትና ባለድርሻ አካላት አመራሮችና ተወካዮች ጋር በአንደኛው ሩብ አመት የቢሮውና የቅንጅታዊ ትስስር የፈጠሩ ተቋማት ዕቅድ አፈፃፀም በተገኙ ጥንካሬዎችና በታዩ ክፍተቶች ዙሪያ የተዘጋጀ ሰነድ ቀርቦ በቤቱ በመገምገም በቀጣይ መከናወን በሚገባቸው ጉዳዮች አቅጣጫዎችን በማመላከት ተካሂዷል

መድረኩን የመሩት የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የሞደርናይዜሽን ዘርፍ ምክትል ቢሮ ሀላፊ መህመድ አብዱራህማን እንደገለፁት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ እንደ ተቋምና ከተለያዩ ተቋማት ጋር በቅንጅትና ተቀራርቦ በመስራት በገቢ አሰባሰቡ የተመዘገበው አፈፃፀም ውጤታማ እንዲሆነ በመጠቆም አገልግሎት አሰጣጡን በማዘመን ቀልጣፋ፣ በቴክኖሎጂ የታገዘ ፣ ወጪ ቆጣቢ፣ ተደራሽ እና ፍትሓዊ እንዲሆን በማድረግ የደንበኞችን እርካታ በመጨመር ቢሮው በበጀት ዐመቱ የመጀመሪያው ሩብ አመት ሊሰበስብ ያቀደውን ገቢ 94 .33 በመቶ እንደ ከተማ ለማሳካት ችሏል ብለዋል ።

በዚህም መሰረት ቢሮው ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር የመግባቢያ የስራ ዕቅድ በማዘጋጀት ወደ ትግበራ ከገባ በኃላ የሚጠበቀውን ገቢ ለመሠብሠብ በበላይነት በቢሮው እንደሚመራ እና ውጤቱንም በከተማ ደረጃ እየተገመገመ መምጣቱ እንዲሁም የታዩ ክፍተቶች በቀጣይ ቀሪ ወራቶች እንዲስተካከል በጥብቅ በመምራትና በመሥራት የታቀደውን ገቢ ለማሳካት የባለድርሻ አካላት የውይይትና የግምገማ መድረክ ወሳኝ እንደሆነም አቶ መሐመድ አመላክተዋል ።

በመድረኩ የተገኙት ባለድርሻ አካላት የቢሮውን ተነሳሽነትና ሪፖርት አቀራረብ በማድነቅ ከተማዋ የምታመነጨውን ኢኮኖሚ በአግባቡና በወቅቱ ለመሠብሰብ እንዲቻል የነበራቸውን ጠንካራና ክፍተቶቾ በመግለፅ በሩብ አመት የተሰበሰበው ገቢ መነሻ የታዩ ክፍተቶችን በቀጣይ አርሞ የበጀት አመቱ ገቢ አሰባሰብ እንዲሳካ እንደተቋማቸው ሚናቸውን በሚገባ እንደሚወጡ አፅንኦት በመሥጠት ተናግረዋል ።

በገቢ አሰባሰቡ ከተቋሙ ጋር ሊኖር የሚገባውን የመረጃ ልውውጥ ቀልጣፋ እና ተደራሽ ለማድረግ የስነ ምግባር ግድፈቶችን እና ብልሹ አሰራሮችን ለመከላከል ፣ የተቋም ግንባታ አፈፃፀሞችን በሚገባ ለመፈፀም እንዲሁም ከተማዋ የምታመነጨውን ገቢ በብቃት ለመሰብሠብ ያስችል ዘንድ የበኩላቸውን ክትትል እና ድጋፍ እንደሚያደርጉና በቀጣይም ከዚህ መነሻ በቁርጠኝነት እንደሚሰሩም ተሳታፊዎቹ አሳስበዋል

የበጀት አመቱን የሩብ አመት የቢሮውንና የቅንጅታዊ ስራዎች አፈፃፀም የተጠቃለለ ዕቅድ ሪፖርት መነሻ የመወያያ ሰነድ በቢሮው የእስታንዳርዳይዜሽንና አገልግሎት አሰጣጥ ዳይሬክተር በአቶ ግርማ አለሙ ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል ፡፡

በውይይቱ ለተነሱ ጥያቄዎች ፣ ሀሳቦችና አስተያየቶች በቢሮው አመራሮችና የስራ ኃላፊዎች ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቷል

ቢሮው የከተማዋን ገቢ በአግባቡና አልቆ ለመሠብሠብ የተሰጠውን ስልጣንና ተግባር ለማስፈፀም የቅንጅታዊ አሰራር የተቀመጡ የገቢ ዕቅዶችን በቀሪ ወራት በቀርጠኝነት ለመፈፀም እንደሚገባ አቅጣጫዎች በአመራሮቹ በአፅንኦት ተቀምጧል ።

በቅንጅትና በትብብር መንፈስ መሥራት ፣ ዘመኑ የደረሰበት የገቢ አሰባሰብ ቴክኖሎጂን በአግባቡ መጠቀም የመዲናዋ የገቢ አሰባሰብ በማሳለጥ የሚታዩ ልማቶችን እውን ማድረግ እንደሚቻልም አመላክተዋል ።

ከተማዋ ያቀደችውን ገቢ ለማሳካት የመረጃ ልውውጥን ማላቅ ፣ በቀሪ ወራት ጠንክሮና ተናቦ መሥራት እንደሚገባ ገልፀው ባለድርሻ አካላት ከተቋማት ጋር በትስስር በመስራት ውጤት ተኮር ተግባራትን በመፈፀም ከአገልግሎት አሰጣጥ ረገድ ችግር ፈቺና የህግ ተገዢነት ማስከበር ተግባራትን ልናከውንና በተጠያቂነት ልንሰራም ይገባል ሲሉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል ፡፡

በመድረኩም ከቢሮው ጋር የስራ ስምምነት ፊርማ በማድረግ ለቅንጅታዊ ስራ ወደ ተግባር የገቡት ተቋማት አዲስ አበባ ፋይናንስ ቢሮ ፣ ንግድ ቢሮ ፣ የፌደራል ገቢዎች ሚኒስቴር ፣ የአዲስ አበባ ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን፣ ኢትዮ ቴሌከም ፣ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፣ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ፣ ኢንፎርሜሽንና መረብ ደህንነት ፣ ህብረት ስራ ኮሚሽን፣ የመንግስት ልማት ድርጅቶች አስተዳደር ባለስልጣን ፣ አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ፣ የመንግስት ግዢና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት፣ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኦሮሚያ ገቢዎች ቢሮ እና ንግድ ቢሮሌሎችም ተቋማት ተገኝተዋል ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *