ጥቅምት 28 ቀን 2018 ዓ / ም ፥ የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ
የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ አገልግሎቱን ዘመናዊና ተደራሽ ለማድረግ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ተገለፀ።
በቢሮው የመረጃ ቴክኖሎጂ ማስተዳደር ዳይሬክተር አቶ አብዱላዚዝ ከሊፋ እንደገለፁት በሁሉም ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች የኢፋይሊንግና የኢፔይመንት ቴክኖሎጂ አገልግሎት እንዲስፋፋ በተሰራው ስራ በቴክኖሎጂ መጠቀም ከሚገባቸው ታክስ ከፋዮች መካከል 70 ከመቶ የሚሆኑት ለመጠቀም መመዝገባቸውን ገልጸዋል ።
አያይዘውም በማኑዋል በመሰጠቱ ምክንያት በከፍተኛ ሁኔታ ለፎርጅጅ ተጋልጦ የነበረው ክሊራንስ አገልግሎት በማስቆም በውስጥ አቅም በለማ ሶፍትዌር መቀየር መቻሉንና የግብር ግዴታቸውን ሳይወጡ ክሊራንስ ሲወስዱ የነበሩ አካላትን ወደ ግብር ስርዓቱ እንዲገቡ እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል ::
በሌላ መልኩ ውስብስብና የግልጽነት ችግር ይታይበት የነበረው የታክስ ዕዳ አስተዳደር ስራ በውስጥ አቅም በለማ ሶፍትዌር አማካይነት ዘመናዊና ግልጽ እንዲሆን ማስቻሉን ገልጸዋል ።
በቀጣይ አጭር ጊዜ ውስጥ ኢ_ፋይል ለሚያደርጉ ግብር ከፋዩች የውሳኔ ስርጭት እና የክሊራንስ ፖርታል ከፌዴራል ገቢዎች ሚኒስቴር ጋር በመተባበር እየተሰራ መሆኑንም ጠቁመዋል
ከህግ ማስከበሩ አንጻር ከኢንሳ ጋር በመተባበር እየተሰራ የሚገኘው ፕሮጀክት እንዲሁም በመጠናቀቅ ላይ የሚገኘው በቪዲዩ፣ በድምጽና በጂፒኤስ የታገዘው የቦዲወርም ካሜራ የቁጥጥር ስራው ግልጽና ፍትሐዊ ለማድረግ በቁጥጥር ሰራተኞች ላይ ተግባራዊ የሚደረግ መሆኑን ገልጸዋል።
ባጠቃላይ ቢሮው አገልግሎቱን ዘመናዊ በማድረጉ ከግብር ከፋዩ ሕብረተሰብ ጋር ያለው ግንኙነት ከማጠናከሩም በላይ የገቢ አሰባሰቡ ግልፅና ተጠያቂነት የተሞላበት እንዲሆን እያደረገ መሆኑን ጠቅሰዋል
በሌላ በኩል የተቋሙን አገልግሎት ዘመናዊና ተደራሽ በመደረጉ ታክስ ከፋዮች ባሉበት ሆነው ግዴታቸው እንዲወጡ ከማድረጉም በላይ ግብር ከፋዮች በራስ ፍላጎት አሳውቆ የመክፈል ባህላቸውን እየተሻሻለ መምጣቱንና የገቢ አሰባሰቡ ውጤታማ እንዳደረገው ገልጸዋል።
