ያለደረሰኝ ግብይት በፈፀሙ 19 የአትክልትና ፍራፍሬ ነጋዴዎች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ ተወሰደ፡፡

ጳጉሜ 1 ቀን 2017ዓ.ም፣ አዲስ አበባ፣ ገቢዎች ቢሮ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በንፋስ ስልክ ላፍቶ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ባካሄደው የደረሰኝ ቁጥጥር ያለደረሰኝ ሲገበያዩ የተገኙ 19 ግብር ከፋዮች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ መወሰዱ ተገልፆል፡፡

የቅርንጫፍ ፅ/ቤቱ የህግ ተገዥነት ዘርፍ ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ዘሪሁን ይልማ እንደገለፁት በዛሬው ዕለት ከለሊት ጀምሮ በላፍቶ አትክልትና ፍራፍሬ የገበያ ማዕከል ቁጥጥር በማካሄድ እርምጃው ተወስዷል፡፡

በገበያ ማዕከሉ የአትክልትና ፍራፍሬ ነጋዴዎች ግብይት በሚፈፅሙበት ወቅት ደረሰኝ መቁረጥ በህግ የሚገደዱ መሆናቸውን ያነሱት ኃላፊው ከዚህ ወጭ የሚካሄድ ግብይት ህገወጥ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ሸማቹ ህብረተሰብም በግብይት ወቅት ደረሰኝ በመጠየቅ እንዲሁም ሻጩ ግብር ከፋይም ለፈፀመው ሽያጭ ደረሰኝ በመስጠት የግብይቱን ጤናማነት ልያረጋግጥ ይገባልም ብለዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *