Tsehay Tadesse

የተጠያቂነት አሰራሮችን በማጠናከር የአገልግሎት አሰጣጥና የመልካም አስተዳደር ችግሮች መቅረፍ እንደሚገባ ተገለፀ፡፡

ህዳር 3 ቀን 2018ዓ.ም ፣ አዲስ አበባ፣ ገቢዎች ቢሮ ይህ የተገለጸው በዛሬው ዕለት የቢሮው የሞደርናይዜሽንና የፅ/ቤት ዘርፎች የበጀት ዓመቱን የ4 ወራት ዕቅድ አፈፃፀሞችን ከቅርንጫፍ የዘርፉ አመራሮች ጋር በገመገሙበት መድረክ ነው፡፡ በመድረኩ የቢሮው የፅ/ቤት ኃላፊ አቶ አዳነ ሱሌ በየደረጃው ያለው አመራር ስራዎችን በአግባቡ በመምራት ውጤት ከማስመዝገብ አኳያ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን ለማረም በትኩረት መስራት ይገባል ብለዋል፡፡ በተለይም ከአገልግሎት…

Read More

ቢሮው ለወረዳ ማይክሮ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት አመራሮች በተሻሻለው የገቢ ግብር አዋጅ ላይ የግንዛቤ ማሰጨበጫ ስልጠና ሰጠ።

ህዳር 1 ቀን 2018ዓም፣ አዲስ አበባ፣ገቢዎች ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ከኔዘርላንድ የልማት ድርጅት ጋር በመተባበር በስሩ ለሚገኙ የወረዳ ማይክሮ ቅ/ፅ/ቤት አመራሮች በተሻሻለው የገቢ ግብር አዋጅ 1395/2017 ላይ ስልጠና ሰጥቷል። የስልጠና መድረኩን በንግግር የከፈቱት የቢሮው የታክስ ጉዳዮች ም/ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ወርቅነሽ ሰቦቃ ቢሮው በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች አቅም ለመገንባት የሚያስችሉ ተግባራት በተከታታይነት እያከናወነ ይገኛል…

Read More

ቢሮው የአገልግሎት አሰጣጡ ዘመናዊ ለማድረግ የሚያግዙ ትላልቅ የቴክኖሎጂ ፕሮጀክቶችን በመቅረፅ ወደ ተግባር እያሸጋገረ መሆኑ ተገለፀ።

ጥቅምት 28 ቀን 2018 ዓ / ም ፥ የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ አገልግሎቱን ዘመናዊና ተደራሽ ለማድረግ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ተገለፀ። በቢሮው የመረጃ ቴክኖሎጂ ማስተዳደር ዳይሬክተር አቶ አብዱላዚዝ ከሊፋ እንደገለፁት በሁሉም ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች የኢፋይሊንግና የኢፔይመንት ቴክኖሎጂ አገልግሎት እንዲስፋፋ በተሰራው ስራ በቴክኖሎጂ መጠቀም ከሚገባቸው ታክስ ከፋዮች መካከል 70 ከመቶ የሚሆኑት ለመጠቀም…

Read More

የታክስ ባለስልጣኑ ግብራቸውን አሳውቀው ያልከፈሉ ግብር ከፋዮች በቀሪዎቹ ጥቂት ቀናቶች ግብራቸውን አሳውቀው በመክፈል የዜግነት ግዴታቸውን እንዲወጡ ጥሪ ማቅረቡ ተገለፀ ።

ጥቅምት 28 /2018 ዓ.ም አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የግብር ከፋዮች ዓመታዊ ግብር አሳውቆ የመክፈያ ጊዜ እየተጠናቀቀ በመሆኑ በከተማዋ ያሉ ግብር ከፋዮች ግብራቸውን በሚከፍሉበት ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቶች በመገኘት በቀሪ ቀናት በመክፈል የግብር መክፈል ኃላፊነታቸዉን እንዲወጡ አሳሰበ ቢሮው ለግብር ከፋዮች ምቹ ፣ ቀልጣፋና ፈጣን የሆኑ አሰራሮችን ዘርግቶ ሲያስተናግድ ቢቆይም የ2017 በጀት…

Read More

በተቋሙ በየደረጃው ያለው አመራርና ፈፃሚ ኃላፊነቱን በአግባቡ በመወጣት የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮች ለመቅረፍ በትኩረት መስራት እንዳለበት ተገለጸ፡፡

ጥቅምት 22 ቀን 2018ዓ.ም፣ አዲስ አበባ ፣ ገቢዎች ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በማዕከል፣ በሁሉም ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶችና ወረዳዎች ከሚገኙ አመራሮችና ፈፃሚዎች ጋር በአገልግሎት አሰጣጥ የሚስተዋሉ ችግሮች ለመቅረፍ የሚያስችል የውይይት መድረክ በማዕከልና በሁሉም ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶቹ አካሄደ፡፡ በውይይት መድረኩ የቢሮው ኃላፊ አቶ ቢኒያም ምክሩ ተቋሙ ፍትሃዊ የግብር አሰባሰብ ስርዓት በማስፈን ተልዕኮውን በአግባቡ ለመወጣት አዳዲስ አሰራሮችንና…

Read More

በየደረጃው ያለው ፈፃሚ የአገልጋይነት ስብእና በመላበስ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መፍታት እንደሚገባ ተገለጸ ፡፡

ጥቅምት 19 / 2018 ዓ.ም አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ። በቢሮው የሰው ኃብት ስራ አመራር ዳይሬክቶሬት አዲስ በተሻሻለው የመንግስት ሰራተኞች አዋጅ ቁጥር 87/2017 ላይ በየደረጃው ለሚገኘው የሰው ኃብት ስራ አመራር ዳይሬክቶሬት ሰራተኞች ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እየሰጠ ነው ፡፡ በቢሮው የቢሮ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አዳነ ሱሌ በግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናው ተገኝተው እንደገለጹት ስልጠናው ለቢሮው ሰራተኞች በዕውቀት…

Read More

ቢሮው ፍትሃዊ የገቢ አሰባሰብን ለማስፈን የሚያደርገው ጥረት ውጤታማነት ለማላቅ የተቋማት ቅንጅት ሊጠናከር እንደሚገባ ተገለፀ ።

ጥቅምት 20 / 2018 ዓ.ም አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ቢሮው የበጀት አመቱን የአንደኛ ሩብ አመት የተቋማትና የባለድርሻ አካላት የቅንጅታዊ ስራዎች አፈፃፀም ግምገማ አካሄደ ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በበጀት ዐመቱ የመጀመሪያው ሩብ አመት ያቀደውን የላቀ ገቢ አሰባሰብ ለማሳካት ከባለድርሻ አካላት ጋር ቅንጅትና ትብብር በማጠናከር ያከናወናቸውን ተግባራት ዛሬ በጥልቀት በመገምገም የቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀምጧል ።…

Read More

በቢሮው የአገልግሎት አሰጣጥ መማክርት ጉባዔ ተቋቋመ ።

ጥቅምት 15 / 2018 ዓ.ም አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ። በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በሚሠጠው አገልግሎት እርካታን ማረጋገጥ ይቻል ዘንድ የአገልግሎት አሰጣጥ መማክርት ጉባዔን በዛሬው ዕለት አቋቁሟል። በዚህ የመማክርት ጉባኤ ምስረታ ላይ 50 የሚሆኑ ከንግድ ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፣ ከሲቪክ ማህበራት፣ ከንግድ ማህበረሰብ ፣ ከተገልጋይ ፣ ከባለድርሻ አካላት ሴክተር ተቋማት ፣ ከገቢዎች…

Read More

የቢሮው የህግ ተገዢነት ዘርፍ የበጀት አመቱን የሩብ አመት የዕቅድ አፈፃፀም በጥልቅ በመገምገም የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን አስቀመጠ ።

ጥቅምት 05 2018 ዓ.ም አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በ2018 በጀት አመት የታቀደውን ገቢ የታክስ ፍትሀዊነት በማረጋገጥ ፣ ከሌብነት ፣ ብልሹ አሰራሮችና የመልካም አስተዳደር ችግሮች በመላቀቅ ገቢን በላቀ ደረጃ ለመሰብሰብ የተለያዩ አሰራሮችን ዘርግቶ ወደ ተግባር መግባቱ ይታወቃል የቢሮው የህግ ተገዢነት ዘርፍ የበጀት አመቱን የሩብ አመት ዕቅድ አፈፃፀሙን ዛሬ ከዳይሬክተሮች…

Read More

የቢሮው የታክስ ዘርፍ የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የገቢ እቅድ አፈፃፀም ግምገማ በማካሄድ የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫዎቹን አስቀመጠ ።

ጥቅምት 5 / 2018 ዓ.ም : አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የቢሮው የታክስ ዘርፍ በበጀት ዓመቱ በመጀመሪያ ሩብ ዓመት አቅዶ ያከናወናቸውን ቁልፍ እና አበይት ተግባራት አፈፃፀሙን ገምግሟል ። የግምገማውን መድረክ የከፈቱት በቢሮው የታክስ ዘርፍ ምክትል ቢሮ ሃላፊ ወ/ ሮ ወርቅነሽ ሰቦቃ ግምገማው በዕቅድ አፈፃፀሙ የታዩትን ጠንካራ እና ደካማ ጎኖች ፣ የተገኙ መልካም ተሞክሮዎች እንዲሁም በቀጣይ ትኩረት…

Read More