በመዲናዋ በሱፍ ልብስ ንግድ ስራ ከ1 ሚሊዮን ብር በላይ ያለደረሰኝ ሽያጭ ሲፈፅሙ የተገኙ 7 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡
የካቲት 15 ቀን 2018ዓ.ም ፣ አዲስ አበባ፣ ገቢዎች ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የግብር ስወራን ለመከላከልና የንግድ ሥርዓቱን ፍትሀዊነት ለማረጋገጥና የህግ የበላይነትን ለማስከበር በተከናወነ የተጠና፣ የተቀናጀና ድንገተኛ ኦፕሬሽን በ5 የሱፍ ልብስ ንግድ ድርጅቶች ደረሰኝ ሳይቆርጡ ግብይት ሲፈጽሙ የተገኙ 7 ተጠርጣሪዎችን በህግ ቁጥጥር ስር ማዋሉን አሳወቀ። ቢሮው የካቲት 14 ቀን 2018ዓ.ም በከተማዋ በተለያዩ አካባቢዎች…
