በመዲናዋ በተሽከርካሪ ጎማዎች ንግድ በተሰማሩ ነጋዴዎች ላይ በተካሄደ የታክስ ኦፕሬሽን በ11 የንግድ ድርጅት ያለደረሰኝ ሽያጭ ሲፈፅሙ የተገኙ 15 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡

ታህሳስ 11 ቀን 2018ዓ.ም ፣ አዲስ አበባ፣ ገቢዎች ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በከተማዋ በተለያዩ አካባቢዎች የተሸከርካሪ ጎማ በሚሸጡ የንግድ ድርጅቶች ላይ ባካሄደው የኦፕሬሽን ተግባር ያለደረሰኝ ሽያጭ ሲፈፅሙ የተገኙ 15 ግለሰቦችን በህግ ቁጥጥር ስር ማዋሉን አሳውቋል፡፡ በዛሬው ዕለት ቢሮው ያካሄደው ድንገተኛ የኦፕሬሽን ተግባር ለረጅም ቀናት በተካሄደ ጥናት ላይ የተመሰረተ ሲሆን በቁጥጥር ስር የዋሉት…

Read More

የተጠያቂነት አሰራሮችን በማጠናከር የአገልግሎት አሰጣጥና የመልካም አስተዳደር ችግሮች መቅረፍ እንደሚገባ ተገለፀ፡፡

ህዳር 3 ቀን 2018ዓ.ም ፣ አዲስ አበባ፣ ገቢዎች ቢሮ ይህ የተገለጸው በዛሬው ዕለት የቢሮው የሞደርናይዜሽንና የፅ/ቤት ዘርፎች የበጀት ዓመቱን የ4 ወራት ዕቅድ አፈፃፀሞችን ከቅርንጫፍ የዘርፉ አመራሮች ጋር በገመገሙበት መድረክ ነው፡፡ በመድረኩ የቢሮው የፅ/ቤት ኃላፊ አቶ አዳነ ሱሌ በየደረጃው ያለው አመራር ስራዎችን በአግባቡ በመምራት ውጤት ከማስመዝገብ አኳያ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን ለማረም በትኩረት መስራት ይገባል ብለዋል፡፡ በተለይም ከአገልግሎት…

Read More

የከተማዋ ገቢ ከለውጡ ወዲህ በየዓመቱ ፈጣን እና እመርታዊ ዕድገት ማሳየቱ ተገለፀ ።

ጳጉሜ 03 / 2017 ዓ.ም አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የነዋሪዋ የልማት ፍላጎትና የከተማዋ ፈጣን ዕድገት ከለውጡ ወዲህ ከአመት አመት በመጨመሩ በገቢ አሰባሰቡ ከፍተኛ እምርታ መምጣቱ ተገለፀ ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የህግ ተገዢነት ዘርፍ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ ሚኪያስ ሙሉጌታ ከቢሮው የኮሙንኬሽን ዳይሬክቶሬት ዝግጅት ክፍል የጳጉሜን 3 ” እምርታ ለዘላቂ ከፍታ ” በሚል…

Read More

ቢሮው ከንግዱ ማህበረሰብና ከግብር ከፋዮች ጋር ተቀራርቦ በመወያየትና በመስራት በገቢው ዘርፍ የሚስተዋሉ ችግሮች ለመፍታት በትኩረት እየሰራ መሆኑ ተገለፀ፡፡

ህዳር 19/3/2018ዓ.ም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ከአዲስ አበባ ከተማ ንግድና ዘርፍ ማሀበራት ም/ቤት የቦርድ አመራሮችና ከ11ንዱም ክፍለ ከተማ የነጋዴ ተወካይ ማህበራት አመራሮች ጋር ይበልጥ ተቀራርቦ ለመስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ውይይት አካሂዷል፡፡ በውይይቱም የንግዱ ማህበረሰብ ተወካዮች ከገቢዎች ቢሮ ከአገልግሎት አሰጣጥና የግብር ከፋይ መስተንግዶ፣ ከደረሰኝ ባለሙያዎች ቁጥጥርና ስነ ምግባር ፣ ከቀን ገቢ ግምት ፣ ከተሻሻለው…

Read More

የሐዋሳ ከተማ ገቢዎች ባለስልጣን ልዑካን ቡድን አባላት ከአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ፍትሃዊ የግብር አሰባሰብ ስርዓት ለመዘርጋት እየተከናወኑ ባሉ ተግባራት ላይ የልምድ ልውውጥ አካሄዱ፡፡

መስከረም 10/ 2018 ዓ.ም : አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የሐዋሳ ከተማ ገቢዎች ባለስልጣን ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት በቢሮው በመገኘት ቢሮው የገቢ አሰባሰብ ሥርዓቱን ቀልጣፋ ፣ ውጤታማ ፣ ከሙስና የፀዳ እና ግቡን ያሳካ እንዲሆን የዘረጋቸው አሰራሮች እና ስትራቴጂዎች ዙሪያ የልምድ ልውውጥ አካሂዷል ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ሃላፊ አቶ ቢኒያም ምክሩ ለቡድኑ የእንኳን ደህና መጣችሁ…

Read More

የቢሮው አመራሮችና ሰራተኞች 18ኛውን የሰንደቅ ዓላማ ቀን‹‹ ሠንደቅ ዓላማችን ለኢትዮጵያ ታላቅ የከፍታ ዘመን ብሥራት፣ ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጲያ ሕዳሴ›› በሚል መረ ቃል አከበሩ፡፡

ጥቅምት 3/2018ዓ.ም፣ አዲስ አበባ፣ ገቢዎች ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ አመራሮችና ሰራተኞች በዛሬው ዕለት በሀገር አቀፍ ደረጃ የተከበረውን 18ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን የብሄራዊ መዝሙር በመዘመርና ቃለ መሀላ በመፈፀም ሥነ-ሥርዓት እንዲሁም በተለያዩ ዝግጅቶች በደማቅ ሁኔታ አክብረው ውለዋል፡፡ በክብረ በዓሉ ላይ ንግግር ያደረጉት የቢሮው ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ አዳኔ ሱሌ የሰንደቅ ዓላማ ቀንን የምናከብረው በእኛ ኢትዮጵያውያን…

Read More

ቢሮው ፍትሃዊ የገቢ አሰባሰብን ለማስፈን የሚያደርገው ጥረት ውጤታማነት ለማላቅ የተቋማት ቅንጅት ሊጠናከር እንደሚገባ ተገለፀ ።

ጥቅምት 20 / 2018 ዓ.ም አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ቢሮው የበጀት አመቱን የአንደኛ ሩብ አመት የተቋማትና የባለድርሻ አካላት የቅንጅታዊ ስራዎች አፈፃፀም ግምገማ አካሄደ ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በበጀት ዐመቱ የመጀመሪያው ሩብ አመት ያቀደውን የላቀ ገቢ አሰባሰብ ለማሳካት ከባለድርሻ አካላት ጋር ቅንጅትና ትብብር በማጠናከር ያከናወናቸውን ተግባራት ዛሬ በጥልቀት በመገምገም የቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀምጧል ።…

Read More

በደረቅ ጭነት ተሽከርካሪዎች ላይ የሚካሄድ የደረሰኝ ቁጥጥር ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገለፀ።

ህዳር 14 ቀን፤2018፣ አዲስ አበባ፣ገቢዎች ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በሁሉም የከተማዋ አቅጣጫዎች ወደ ከተማዋ የሚገቡ፣ከከተማዋ የሚወጡና በከተማዋ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪዎች ፣ሚኒባሶችና አነስተኛ ሽፍን መኪኖች ላይ የመኪና ኦፕሬሽን ስራዎች ማጠናከሩ ገልጿል። በዚህም ያለደረሰኝ የሚካሄዶ የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪዎች ላይ የህግ ተጠያቂነት በአሸከርካሪዎች ላይ ጭምር እንዲሰፍን እያደረገ መሆኑ አሳውቋል። በአሁኑ ወቅት የደረሰኝ ቁጥጥሩ…

Read More

የቢሮው የታክስ ዘርፍ የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የገቢ እቅድ አፈፃፀም ግምገማ በማካሄድ የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫዎቹን አስቀመጠ ።

ጥቅምት 5 / 2018 ዓ.ም : አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የቢሮው የታክስ ዘርፍ በበጀት ዓመቱ በመጀመሪያ ሩብ ዓመት አቅዶ ያከናወናቸውን ቁልፍ እና አበይት ተግባራት አፈፃፀሙን ገምግሟል ። የግምገማውን መድረክ የከፈቱት በቢሮው የታክስ ዘርፍ ምክትል ቢሮ ሃላፊ ወ/ ሮ ወርቅነሽ ሰቦቃ ግምገማው በዕቅድ አፈፃፀሙ የታዩትን ጠንካራ እና ደካማ ጎኖች ፣ የተገኙ መልካም ተሞክሮዎች እንዲሁም በቀጣይ ትኩረት…

Read More

ያለደረሰኝ ግብይት በፈፀሙ 19 የአትክልትና ፍራፍሬ ነጋዴዎች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ ተወሰደ፡፡

ጳጉሜ 1 ቀን 2017ዓ.ም፣ አዲስ አበባ፣ ገቢዎች ቢሮ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በንፋስ ስልክ ላፍቶ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ባካሄደው የደረሰኝ ቁጥጥር ያለደረሰኝ ሲገበያዩ የተገኙ 19 ግብር ከፋዮች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ መወሰዱ ተገልፆል፡፡ የቅርንጫፍ ፅ/ቤቱ የህግ ተገዥነት ዘርፍ ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ዘሪሁን ይልማ እንደገለፁት በዛሬው ዕለት ከለሊት…

Read More