በደረቅ ጭነት ተሽከርካሪዎች ላይ የሚካሄድ የደረሰኝ ቁጥጥር ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገለፀ።

ህዳር 14 ቀን፤2018፣ አዲስ አበባ፣ገቢዎች ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በሁሉም የከተማዋ አቅጣጫዎች ወደ ከተማዋ የሚገቡ፣ከከተማዋ የሚወጡና በከተማዋ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪዎች ፣ሚኒባሶችና አነስተኛ ሽፍን መኪኖች ላይ የመኪና ኦፕሬሽን ስራዎች ማጠናከሩ ገልጿል።

በዚህም ያለደረሰኝ የሚካሄዶ የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪዎች ላይ የህግ ተጠያቂነት በአሸከርካሪዎች ላይ ጭምር እንዲሰፍን እያደረገ መሆኑ አሳውቋል።

በአሁኑ ወቅት የደረሰኝ ቁጥጥሩ በቀን ብቻም ሳይሆን በለሊት ጭምር ተጠናክሮ መቀጠሉ ያሳወቀ ሲሆን ደረሰኝ ሳይዙ ሸቀጦች ይዘው በተንቀሳቀሱ ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ ወስጃለው ብሏል።

ቢሮው የቁጥጥር ስራውን በየደረጃው ከተቋቋሙ ግብረ ሀይሎች ጋር በመቀናጀት እያከናወነ ሲሆን በዚህም ተሸከርካሪዎች ዕለታዊ ደረሰኝ ሳይዙ በከተማዋ ውስጥ ሲንቀሳቀሱ፣ከከተማው ሲወጡ ተገኝተው አስተዳደራዊ የቅጣት እርምጃ ከመውሰድ በተጨማሪ ለእያንዳንዱ ለጫኑት ሸቀጥ ደረሰኝ እንዲቆርጡ ተደርጓልም ብሏል።

በቀጣይም በከተማዋ ጭነት የጫኑ ማንኛውም አይነት ተሽከርካሪዎች፣ ለጫኑት ሸቀጥ ደረሰኝ እንዲቆርጡ ብቻም ሳይሆን አሽከርካሪዎቻቸው ላይም የህግ ተጠያቂነት እንዲሰፍን የሚደረግ መሆኑ አብራርቷል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *