ቢሮው ለወረዳ ማይክሮ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት አመራሮች በተሻሻለው የገቢ ግብር አዋጅ ላይ የግንዛቤ ማሰጨበጫ ስልጠና ሰጠ።

ህዳር 1 ቀን 2018ዓም፣ አዲስ አበባ፣ገቢዎች ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ከኔዘርላንድ የልማት ድርጅት ጋር በመተባበር በስሩ ለሚገኙ የወረዳ ማይክሮ ቅ/ፅ/ቤት አመራሮች በተሻሻለው የገቢ ግብር አዋጅ 1395/2017 ላይ ስልጠና ሰጥቷል።

የስልጠና መድረኩን በንግግር የከፈቱት የቢሮው የታክስ ጉዳዮች ም/ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ወርቅነሽ ሰቦቃ ቢሮው በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች አቅም ለመገንባት የሚያስችሉ ተግባራት በተከታታይነት እያከናወነ ይገኛል ብለዋል።

ቢሮው የተሰጠውን ፍትሃዊ ገቢ የመሰብሰብ ተልዕኮ ሊሳካ የሚችለው ብቃትያለው አመራርና ፈፃሚ መገንባት ሲቻል እንደሆነ የገለፁት ም/ቢሮ ኃላፊዋ የዕለቱ ስልጠናም በተሻሻለው የገቢ ግብር አዋጅ ላይ ለወረዳ አመራሩ ግልፅ ግንዛቤ ለመጨበጥ ታስቦ መዘጋጀቱን ተናግረዋል።

በመድረኩ በገንዘብ ሚኒስቴር የታክስ ጉዳዮች አማካሪ አቶ ዋሲሁን አባተ በአዲሱ የፌዴራል ገቢ ግብር አዋጅ ማሻሻያ 1395/2017 ላይ ስልጠና የተሰጠ ሲሆን በተሳታፊዎችም ውይይት ተካሂዷል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *