ታህሳስ 11 /2018 ዓ.ም :አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ
የቢሮው ሞደርናይዜሽን ዘርፍ በበጀት ዓመቱ 5ወራት ውስጥ በ179 ሰራተኞች ላይ የዲስፕሊን እርምጃ መወሰዱን ገልጿል ።
በቢሮው የሞደርናይዜሽን ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ መሀመድ አብዱራህማን በዕቅድ አፈፃፀም ውይይቱ በበጀት ዓመቱ የተሰሩ ስራዎች ፣ ያጋጠሙ ችግሮችና የተወሰዱ መፍትሄዎች እንዲሁም የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ አስቀምጠዋል ።
አያይዘውም ከዋና መስራያ ቤት አንስቶ በሁሉም ቅርንጫፎች እና ወረዳዎች ጽህፈት ቤቶች ከሌብነትና ብልሹ አሰራር ፣ ከአገልግሎት አሰጣጥ ፣ ከስነ_ምግባር አኳያ ክትትልና ድጋፍ በሰርቪላንስ ካሜራ ፣ በምስለ ተገልጋይና በዕቅድ አፈፃፀም ዙሪያ ተደርጓልም ብለዋል ።
በዚህም ሃላፊነታቸው በአግባቡ ተወጥተው ባልተገኙ 20 አመራሮችና 159 ፈፃሚዎች ላይ የዲስፕሊን እርምጃ መወሰዱን ገልፀዋል ።
አክለውም በቀጣይ የክትትልና ድጋፍ ስራው የሚቀጥል መሆኑን ጠቁመው በአገልግሎት አሰጣጥ ፣ በሀርሞናይዜሽን ፣ በቲን ቁጥር አሰጣጥ ፣ በኢ_ፋይልና ኢ_ፔመንት ፣ በመዝጊያ ኪሊራንስ እንዲሁም በመማክርት ጉባኤን ውይይት የተጠናከረ ስራዎችን በመስራት ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት እንደሚገባ አሳስበዋል ።
የቢሮው ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ አዳነ ሱሌ በበኩላቸው የሚሰጡ አገልግሎቶችን የጥራት ደረጃ በማሳደግ ገቢን በፍትሃዊነት መሰብሰብ ይገባል ብለዋል ።
አያይዘውም የከተማዋን የትኩረት ነጥቦችን የጋራ እውቀት በማድረግ አገልግሎት ጠያቂው ካለምንም እንግልት አገልግሎት የሚያገኝበትን ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠር በየደረጃው ያለ አመራር ኃላፊነት መሆኑን አስገንዝበዋል ።
ውጤታማ የገቢ አሰባሰብ ለአዲስ አበባ ብልጽግና !
