በመዲናዋ ባለፉት አራት ወራት ከ5 ሺህ በላይ የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪዎች ላይ የደረሰኝ ቁጥጥር በመካሄድ ከ954 ሚሊዮን ብር በላይ ደረሰኝ እንዲቆረጥ መደረጉ ተገለፀ።
ህዳር 17 ቀን፤2018፣ አዲስ አበባ፣ገቢዎች ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት አራት ወራት በ5 ሺህ 203 የደረቅ ጭነት ተሸከርካሪዎች ላይ የደረሰኝ ቁጥጥር ማካሄዱ ተገልፆል፡፡ የደረሰኝ ቁጥጥሩ በሁሉም የከተማዋ አቅጣጫዎች ወደ ከተማዋ በሚገቡ፣ከከተማዋ በሚወጡና በከተማዋ ውስጥ በሚንቀሳቀሱ የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪዎች ፣ሚኒባሶችና አነስተኛ ሽፍን መኪኖች ላይ ነው የተካሄደው፡፡ በዚህም ያለደረሰኝ ጭነት በመያዝ ሲንቀሳቀሱ…
