ቢሮው በ2017 በጀት ዓመት ቀጣይ ስድስት ወራት የተጀመሩ የሪፎርም ስራዎችን በማጠናከርና የአገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል በትኩረት እንደሚሰራ ገለጸ ።

ቢሮው በ2017 በጀት ዓመት ቀጣይ ስድስት ወራት የተጀመሩ የሪፎርም ስራዎችን በማጠናከርና የአገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል በትኩረት እንደሚሰራ ገለጸ ።

ጥር 17 / 2017 ዓ.ም አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የበጀት አመቱን የ6 ወራት የገቢ ዕቅድ አፈፃፀሙን ከዋና መስሪያ ቤት ሰራተኞች ገመገመ ።

መድረኩን የቢሮ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አዳነ ሱሌ እንደገለፁት ቢሮው ለታክስ ከፋዩ ሕብረተሰብ የተሳለጠ አገልግሎት የመስጠት ስራ በትኩረት እንደሚሰራና የታክስ አሰባሰብ ሒደቱ አመለካከቱና ክሕሎቱ በተለወጠ አመራርና ባለሙያ እንዲፈጸም የሰው ኃይል የማሟላት ስራው እንዲሁም ከአደረጃጀት ፣ ከሰው ሀይል ሪፎርም፣ ምቹ የስራ አካባቢ መፍጠርና የአገልግሎት አሰጣጥን የማዘመን ፣ የተጀመሩ የቁጥጥር ስራዎችን ይበልጥ የማጠናከር ፣ የሌብነት ፣ ብልሹ አሰራርና የታክስ ስወራን የመታገል እንዲሁም የህግ ተገዢነትን የማስፈን ስራዎች ትኩረት እንደሚሰጣቸው ገልጸዋል ።

አያይዘውም ቢሮው የገቢ አሰባሰቡን ውጤታማና ፍትሐዊ እንዲሆን የአደረጃጀት ፣ የአሰራር እና የሰው ኃይል ችግሮችን እየፈታ መሆኑና ጠንካራ የክትትልና ድጋፍ ስራዎችን እያደረገ መሆኑን ጠቁመው እስካሁን በተሰሩ ስራዎች በተለይም በህዳርና ታህሳስ ወራት የተሻለ ገቢ አፈጻጸም በማስመዝገብ የተሰሩ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን ማሳያ መሆናቸውን አብራርተዋል ፡፡

ቢሮው በቀጣይ 6 ወራት ተቋም መገንባት ላይ በትኩረት እንደሚሰራ የገለጹት በቢሮው የሞደርናይዜሽን ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ መሐመድ ከአደረጃጀት ፣ ከአሰራርና ከቴክኖሎጂ ጋር በተያያዘ የሚታዩ ክፍተቶችን ደረጃ በደረጃ የመፍታት ስራ እንደሚሰሩና ከዚህ ቀደም የተፈጠሩ አደረጃጀቶችና የተዘረጉ አሰራሮች ያመጡት ውጤት የመፈተሸ ስራም እንደሚሰራም ገልጸዋል ፡፡

የተገልጋይ እርካታን ለማረጋረጥ አመላካቾችን መሰረት በማድረግ እንደሚጠኑና የገቢ ሪፎርምን ማረጋገጥ እንዲቻል የቴክኖሎጂን ስራ ትኩረት እንደሚሰጠው ፣ አገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል የተቀመጡ ስታንዳርዶችን ውጤታማ የማድረግ እንዲሁም የውስጥና የውጭ ቅንጅትን በማጠናከር የገቢ አሠባሰቡን ውጤታማ እንዲሆን በትኩረት እንደሚሰራ ኃላፊው ጠቁመዋል ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *