ቢሮው በከተማ አስተዳደሩ የታቀዱ የልማት ተግባራት በላቀ የገቢ አፈፃፀም ለመደገፍ በትኩረት እየሰራ መሆኑ ተገለፀ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በከተማ አስተዳደሩ የታቀዱ የልማት ተግባራት በላቀ የገቢ አፈፃፀም ለመደገፍ በትኩረት እየሰራ መሆኑ ተገለፀ።
የቢሮው የታክስ ጉዳዮች ዘርፍ ም/ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ወርቅነሽ ሰቦቃ የዘርፉን የ2017 ግማሽ በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ከክፍለ ከተማና ከወረዳ የዘርፉ አመራሮችና የስራ ሂደቶች ጋር ገምግመዋል።
በመድረኩም በተሰጠ ማጠቃለያ በአሁኑ ወቅት ከተማዋ የሚያስፈልጋት ዘርፈ ብዙ የልማት ወጪዎች ብቃት ባለው የገቢ አሰባሰብ በመደገፍ የመሸፈን ኃላፊነት የገቢ ሰብሳቢው መስሪያ ቤት ነው ብለዋል።
ከዚህ አኳያ የከተማ አስተዳደሩ የህብረተሰቡን የልማት ፍላጎቶችና ጥያቄዎች ለመመለስና የሰው ተኮር ፕሮጀክቶች ለማሳካት በርካታ ተግባራትን እያከናወነ እንደሆነ የገለፁት ኃላፊዋ ያለ ገቢ ልማት ሊኖር እንደማይችል በማመን የተሰጠ ተልዕኮ በአግባቡ መወጣት እንደሚገባ ተናግረዋል።
ከዚህ አኳያ የበጀት ዓመቱ የገቢ አሰባሰው ውጤቴማነት ካለፉት ጊዜያት አኳያ የተሻለ ቢሆንም ከተማዋ ካላት የገቢ አቅም አኳያ በቀጣይ ይበልጥ ማጠናከር ይጠይቃል ብለዋል።
በግማሽ በጀት ዓመቱ አፈፃፀም የገቢ አሰባሰብ ዕቅድ አፈፃፀሙ አንድ ጊዜ ሞቅ ሌላ ጊዘ ቀዝቀዝ የሚል አፈፃፀም የሚስተዋልበት ነው ያሉት ወ/ሮ ወርቅነሽ የተያዘው ዕቅድ በተሟላ ደረጃ ለማሳካት ከዚህ ቀደም ከነበሩ የተለመዱ አተገባበሮች ወጣ ባለ መልኩ አፈፃፀሞችን በወጥነት ማስቀጠልም ይገባል ብለዋል።
በሌላ በኩልም በተቋሙ በአገልግሎት አሰጣጥ የሚስተዋሉ ችግሮችን በቅርበት በመከታተል መፍታትም ይገባል ብለዋል።
ከልብነትና ብልሹ አሰራሮች ጋር በተገናኘም የሚስተዋሉ ችግሮች በትኩሰት በመፈፀም ማረም እንደሚገባ አሳስበዋል።
በመድረኩ የቢሮው ጨምሮ የአራዳና የንፋስ ስልክ ክፍለ ከተሞች፣የአዲስ አበባ ቁጥር 1 እና የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች የበጀት ዓመቱ የ6 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖሮቶች ቀርበው ውይይት የተካሄደባቸው ሲሆን በመድረኩ ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች የሚመለከታቸው የቅርንጫፍ የዘርፍ ኃላፊዎችና የማዕከል ዳይሬክተሮች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።