ቢሮው ባለፉት 6 ወራት ወቅታዊ መረጃ ለህብረተሰቡ እንዲደርስ በቅንጅት በፈፀማቸው ተግባራት እውቅና አግኝቷል።
ጥር 21/2017ዓም፣ አዲስ አበባ፣ ገቢዎች ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በ2017 ግማሽ በጀት ዓመት ከኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ጋር በቅንጅት ወቅታዊ መረጃ ወደህብረተሰቡ እንዲደር በማድረግ ለማከናወን በቻላቸው ተግባራት እውቅና አግኝቷል።
ቢሮው በቅንጅታዊ አሰራር ለማበርከት በቻለው ከፍተኛ አስተዋፅኦ እውቅና የተሰጠው ከኮሙኑኬሾን ጉዳዮች ቢሮ ነው።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በከተማችን ፍትሃዊ፣ተደራሽና ዘመናዊ የገቢ አሰባሰብ ስርዓት በመዘርጋት የከተማዋ የወጪ ፍላጎት በውስጥ አቅም እንዲሸፈን እየተጋ የሚኝ እንዲሁም በህብረተሰቡ ውስጥ ግብር የመክፈል ባህል ለማዳበር የሜኒስትሪምና የሶሻል ሚዲያዎች አቀናጅቶ በመጠቀም ላይ የሚገኝ ተቋመ መሆኑ ይታወቃል።