ቢሮው በ2017 በጀት ዓመት በስራ አፈፃፀም እና በመንግስት አገልግሎት አሰጣጥ ውጤታማነት ከፍተኛ አፈፃፀም ለማስመዝገብ ቅርንጫፍ ጽ/ ቤቶች ዕውቅና ሽልማት ሰጠ ፡፡

ነሀሴ 19 / 2018 ዓ.ም ፡ አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ

የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ በጀት ዓመት በቁልፍ ግቦች የስራ አፈጻጸም እና በመንግስት አገልግሎት አሰጣጥ ውጤታማነት እንዲሁም ለገቢ አሰባሰቡ የላቀ አስተዋፅኦ ላበረከቱ ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች ዕውቅና ሰጥቷል ፡፡

የዕውቅናና ሽልማት ስነ ስርዓቱ ዓላማም የ2017 ጥንካሬዎችን ይበልጥ አጠናክሮ ለማስቀጠልና ድክመቶችን በማረም የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድን በተሻለ አፈፃፀም ማሳካት መሆኑ ተጠቁሟል።

በመድረኩ የቢሮው ሃላፊ አቶ ቢኒያም ምክሩ በ2018 በጀት ዓመት ከባለፈው በተሻለ መንገድ በመስራት ያደገና የተሻሻለ ገቢ አሰባሰብን በማጠናከር የከተማዋን ጥያቄ በበቂ ለመመለስ ከስራ ሰዓት አጠቃቀም ፣ ከአገልግሎት አሰጣጥ ፣ ከሌብነትና ብልሹ አሰራር ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ችግሮች ለይቶ በማውጣትና በመተጋገል እንዲሁም ከቢሮው የሚወርዱ አሰራሮችን በአግባቡ በመተግበርና ወደ ውጤት በመቀየር ተጨባጭ ለውጥ ማስመዝገብ እንደሚገባ አሳስበዋል ።

የመመዘኛው መስፈርት እና ሂደት በቢሮው የሞደርናይዤሽንና ኮርፖሬት ስራዎች ዘርፍ ምክትል ቢሮ ሃላፊ አቶ መሀመድ አብዱራህማን ቀርቧል ።

በቢሮው በተካሄደው በዚሁ ምዘና 16ቱም ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች ከፍተኛ አፈፃፀም ለማስመዝገብ በመቻል እውቅና ተሰጥቷቸዋል።

ከቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች መካከልም ከ85 % በላይ ያመጡ ሰርተፊኬትና ክሪስታል ዋንጫ የተበረከተ ሲሆን ከፍተኛ ግብር ከፋዮ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የ1ኛ፣ ንፋስ ስልክ ላፍቶና ለሚኩራ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ፅ/ቤቶች 2ተኛና 3ተኛ በመውጣት የሰርተፊኬትና የክሪስታል ዋንጫ ተሸላሚ ሆነዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *