በ2018 በጀት ዓመት ለግብር ከፋዩ ሕብረሰብ የተሳለጠ አገልግሎት መስጠት የተቋሙ አንዱ ቁልፍ ጉዳይ መሆኑን ተገለጸ ።

ነሐሴ 26 ቀን 2017 ዓ / ም የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ

በ2018 በጀት ዓመት በተቋሙ የቴክኖሎጂ አቅርቦትና አጠቃቀምን በማሳደግና በ2017 በጀት ዓመት የተዘረጉ የአሰራር ስርዓቶችን ውጤታማ በሆነ መንገድ ተግባራዊ በማድረግ ለታክስ ከፋዩ ሕብረተሰብ ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት የሞት ሽረት ጉዳይ መሆኑን ተገለጸ ፡፡ይህንን የተገለጸው በቢሮው የሞደርናይዜሽንና ኮርፖሬት ዘርፍ አመራሮች በዘርፉ የ2018 በጀት አመት ዕቅድ ዙሪያ ውይይት ባደረጉበት ወቅት ነው ፡፡የውይይት መድረኩን የመሩት በቢሮው የሞደርናይዜሽን ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ መሐመድ አብዱራሕማ እንደገለጹት ቢሮው በ2017 በጀት ዓመት በቢሮው የታዩ የነበሩ ከአሰራር፣ ከአደረጃጀት ፣ ከሰው ኃይልና ከቴክኖሎጂ ጋር በተያያዘ የነበሩ ችግሮችን የማስተካከል ስራ መሰራቱን ገልጸዋል ፡፡በየደረጃው የሚገኘው አመራርና ፈጻሚ በ2017 በጀት አመት የተዘረጉ አሰራሮችና አደረጃጀቶች ውጤታማ በማድረግ ለተገልጋዩ ሕብረተሰብ የላቀ የአገልግሎት ከመስጠት ባሻገር ሌብነትና ብልሹ አሰራሮችን ማክሰም በትኩረት መስራት እንዳለበትም አሳስበዋል ፡፡አያይዘውም በ2017 በጀት ዓመት የነበሩ ጠንካራ ጎኖችን በማስቀጠል እንዲሁም የነበሩ ውስንነቶችን በማረም የገቢ አሰባሰቡን ውጤታማ ለማድረግ ከመቼውም ጊዜ በላይ ልዩ ትኩረት በመስጠት እንዲሁም በተነሳሽነትና በቁርጠኝነት መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል ፡፡በመድረኩም የዘርፉን የ2018 በጀት ዓመት እቅድ በዝርዝር ቀርቦ ውይይት የተደረገበት ሲሆን ከተሳታፊዎች ጥያቄዎችና አስተያየቶች ቀርበው በኃላፊው ምላሽ ተሰጥቷል ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *