የልደታ ክፍለ ከተማ አነስኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ዕለታዊ ደረሰኝ ሳይዙ ልዩ ልዩ ሸቀቶች ከቦታ ቦታ ሲያዘዋውሩ በተገኙ 26 ተሸክርካሪዎች ላይ ቁጥጥር ማድረጉ ገለፀ።

ነሀሴ 26/ 2017 ዓ.ም : አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ወደ ከተማዋ የሚገቡና የሚወጡ እንዲሁም በከተማዋ ከቦታ ወደ ቦታ የሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎች ለጫኑት ጭነት ህጋዊ ደረሰኝ ስለመያዛቸው ቁጥጥር የማድረግ ስራ ቀን በቀን ተጠናክሮ ቀጥሏል ።

በዛሬው ዕለትም በአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የልደታ ክፍለ ከተማ አነስኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት በመኪናዎች ላይ የቁጥጥር ስራውን አጠናክሮ መቀጠሉን ለዝግጅት ክፍላችን ገልጿል ።

ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቱ የተሽከርካሪ ላይ ኦፕሬሽንና ቁጥጥር ስራን ከጀመረበትጊዜ ጀምሮ እስካሁን በ26 ተሽከርካሪዎች ላይ በዕለቱ የተቆረጡ ደረሰኞች ስለመሆናቸው ቁጥጥሩን አካሂዷል ።

መኪኖቹ ደረሰኝ ባልቆረጡት ላይ አስተዳደራዊ ቅጣት የተቀጡ ሲሆን በቁጥጥሩ ወቅት አሽከርካሪዎቹ የኮንስትራክሽን ግብአቶች ፣ የመኪና ጎማ ፣ የለስላሳ መጠጦችና ሌሎችም ሸቀጣ ሸቀጦች የጫኑ መሆናቸው ተመላክቷል

በመሆኑም የተሽከርካሪ ባለቤትና አሽከርካሪ እንዲሁም ነጋዴ በተሽከርካሪዎች ላይ ጭኖ ለሚያጓጉዘው ማንኛውም ጭነት የጭነቱ ዋጋ ህጋዊ ደረሰኝ ፣ የተቆረጠው ደሰረኝ ከባለንግድ ፍቃዱ ጋር ተመሳሳይ የሆነ ፣ የመጋዘን ፍቃድ ፣ የንግድ ፍቃድ ከመጋዘን ፍቃድ ጋር ተመሳሳይ የሆነ ፣ የማጓጓዣ ( ደሊቨሪ ) ደረሰኝ እንዲሁም የንግድ ፍቃዱ የክፍለሀገር ከሆነ እዚህ ለመሸጥ የንግድ ፍቃድ ያስጠቀሰ መሆኑን የሚያሳዩ ማስረጃዎች መያዝ እንደሚገባው ቢሮው በጥብቅ ያሳስባል ።

የመኪና ላይ ህጋዊ የግብይት ደረሰኝ ቁጥጥር በመዲናዋ በሁሉም ቦታ ቀን በቀን ተጠናክሮ መቀጠሉን ቢሮው አስታውቋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *