መስከረም 11 ቀን 2018 ዓ / ም የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ
የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት ፍትሃዊ የገቢ አሰባሰብ ስርዓት ለመዘርጋት የሚያስችሉ 24 አሰራሮች በጥናት በመለየት ወደተግባር ማሸጋገሩ ይታወቃል።
በዛሬው ዕለትም በየደረጃው ለሚገኙ የሞደርናይዜሽን ዘርፍ የወረዳ ጽሕፈት ቤት ኃላፊዎች፣ የሚመለከታቸው የዋና መስሪያ ቤትና የቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ስራ ሂደትና የቡድን አስተባባሪዎች በተሻሻሉ አሰራሮች ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል።
በቢሮው የሞደርናይዜሽንና ኮርፖሬት ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ መሐመድ አብዱራሕማን ቢሮው ግብርን በፍትሃዊነትና በብቃት የመሰብሰብ ኃላፊነቱን መወጣት እንዲችል የአደረጃጀት፣ የአሰራር፣ የሰው ኃብትና የቴክኖጂ ችግሮችን በመፈተሽ ማስተካከያ እያደረገ ነው ብለዋል።
የዕለቱ መድረክ ዓላማም ከክሊራስ አገልግሎት ጋር በተያያዘ ከስነ ምግባር ጉድለትና የተዘረጉ አሰራሮች በአግባቡ ካለመተግበር በመነጨ የሚነሱ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመቅረፍ የሚያስችል መግባባት መፍጠር መሆኑን ገልፀዋል።
ከክሊራስ አሰጣጥ ጋር በተያያዘ በአገልግሎት አሰጣጥ የሚነሱ ችግሮች ለመቅረፍ የተጠያቂነት አሰራር መዘርጋቱንም ጠቁመዋል።
በመጨረሻም የስልጠናው ተሳታፊዎች ስልጠናው በአግባቡ በመከታተል የታክስ ክሊራንስ የምስክር ወረቀት አሰጣጥ አገልግሎትን ጨምሮ ሌሎች አሰራሮችን ወደ ተግባር በመቀየር በታክስ ከፋዩ ሕብረተሰብ የሚነሱ ችግሮችን መፍታት እንዳለባቸው አሳስበዋል ፡፡
የደንበኞች መስተንግዶና ድጋፍ አገልግሎት ዳይሬክተር ወ/ሮ አስቴር ዘውዴ በበኩላቸው የታክስ ክሊራንስ አገልግሎትን ለታክስ ከፋዩ ቀልጣፋና ውጤታማ በሆነ መልኩ ለመስጠት በተሻሻሉ አሰራሮች ላይ ተገቢውን ግንዛቤ መጨበጥ ይገባል ብለዋል።
አያይዘውም የሪከርድና ማህደር አገልግሎት በየደረጃው ትኩረት ሊሰጠው የሚገባና ስራው በአንድ ክፍል ብቻ የሚተው ሳይሆን የሁሉም ዘርፎች / ክፍሎች ተሳትፎ የሚጠይቅና ወሳኝ ክፍል መሆኑን ጠቅሰዋል ፡፡
የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮን በመወከል የተገኙት በቢሮው የንግድ ኢንስፔክሽንና ሪጎላቶሪ ዳይሬክተር አቶ ዮሴፍ አሰፋ በበኩላቸው የገቢ አሰባሰቡ ውጤታማ እንዲሆን የባለድርሻ አካላት ቅንጅት ወሳኝ መሆኑንና ሁለቱም ተቋማት ያላቸውን ግንኙነት ይበልጥ በማጠናከር ከክሊራንስ አገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ የሚነሱ ችግሮችን መፍታት እንዳለባቸው በመጥቀስ
አያይዘውም ቢሮው አገልግሎቱን ለማዘመን ከዘረጋቸው ቴክኖሎጂዎች በተለይም በኢ ትሬድ ሲስተም ዙሪያ ማብራሪያ በመስጠት ከታሳታፊዎች የቀረቡላቸውን ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል ፡፡