መስከረም 10/ 2018 ዓ.ም : አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ
የሐዋሳ ከተማ ገቢዎች ባለስልጣን ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት በቢሮው በመገኘት ቢሮው የገቢ አሰባሰብ ሥርዓቱን ቀልጣፋ ፣ ውጤታማ ፣ ከሙስና የፀዳ እና ግቡን ያሳካ እንዲሆን የዘረጋቸው አሰራሮች እና ስትራቴጂዎች ዙሪያ የልምድ ልውውጥ አካሂዷል ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ሃላፊ አቶ ቢኒያም ምክሩ ለቡድኑ የእንኳን ደህና መጣችሁ በማለት እንግዶቹን የተቀበሉ ሲሆን የቢሮው የሞደርናይዤሽን ኮርፖሬት ዘርፍ ምክትል ቢሮ ሃላፊ አቶ መሀመድ አብድራህማን ከሚመለከታቸው የቢሮ ዳይሬክቶሬቶች ጋር በመሆን ለልዑካን ቡድኑ ተሞክሮ አጋርተዋል፡፡
ቢሮው ከብልሹ አሰራር የፀዳ፣ ፍትሃዊ የግብር አሰባሰብ ስርዓት ለመዘርጋት የሪፎርም ስራዎችን የማጠናከር ፣ አዳዲስ የአሰራር ስርአቶችን የመዘርጋት ፣ የተሻሻለ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን የማበልፀግ ፣ የመጠቀምና ውጤታማ የማድረግ ፣ የገቢ መሰረትን የማስፋት፣የህግ ተገዢነት የማጎልበትና የቁጥጥር ስራዎችን የማጠናከር ተግባራት ላይ ትኩረት በመስጠት እየሰራ እንደሚገኝ አንስተዋል፡፡
የልዑካን ቡድኑ በዛሬው ዕለትም በንፋስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት በመገኘት የልምድ ልውውጥ አካሂዷል፡፡
በሐዋሳ ከተማ ገቢዎች ባለስልጣን ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ መልኩ ማርቆስ ቢሮው ከዓመት ዓመት እያስመዘገበዉ ያለው የገቢ አሰባሰብ አዳጊ መሆኑ ትኩረታቸውን የሳበ መሆኑን ጠቅሰዋል ።
ገቢው የተሻሻለ እንዲሆን ያስቻሉ በቢሮው የተዘረጉ አዳዲስ አደረጃጀቶች እና አሰራሮች በመመልከታችን ጥሩ ተሞክሮና ለሚቀጥለው ስራችን ትልቅ አቅም ፈጥሮልናል ሲሉም ተናግረዋል ።