በዓላትን በጋራ እናክብር” በሚል መሪ ሀሳብ በሚከበሩት የመስቀል/ደመራ እና የእሬቻ በዓላት አከባበር ዙሪያ ውይይት አካሄዱ።
መስከረም 10 / 2018 ዓ.ም አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ አመራርና ሰራተኞች በአደባባይ በሚከበሩት በዐላት ዙሪያ በቂ ግንዛቤ ይዞ እንዲያከብር የሚያስችል የመወያያ ሰነድ በቢሮው የታክስ ኢንተለጀንሲ ዳይሬክተር በአቶ ተስፋዬ ነጋሽ ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል።
የመስቀል ደመራና የእሬቻ በዓላት በዋናነት በአደባባይ የሚከበሩ በዓላት በመሆናቸው በልዩ ልዩ ከንውኖች ፣ሃይማኖታዊና ባህላዊ እስቱን በጠበቀ መልኩ በድምቀት ይከበራል ።
ዘንድሮ የሚከበሩት መስቀል/ ደመራ እና የእሬቻ በዓል በትላልቅ ድሎች ውስጥ ታጅበው የሚከበሩ በመሆኑ የበዐላቱን እሴቶቹንና ትውፊቱን በጠበቀ መልኩ በአብሮነት መንፈስ ከተለመደው በላይ ርቀት በመሄድ በመደመር መንፈስ በጋራ ወንድማማችነት/ እህትማማችነት ስሜት ማክበር እንደሚገባ ተመላክቷል ።
መዲናችን አዲስ አበባ የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች መቀመጫ በመሆኗ የዘንድሮውን የመስቀል/ደመራና ኢሬቻ በዓላትን ስናከብር ሀገራችን በርካታ ስኬቶችን በማስመዝገብ ወደ ማንስራራት የተሸጋገረችበት መሆኑና ከተማችን በበርካታ ድልች ያታጀቡ የልማት ስራዎችን ያሳካችበትና በርካታ እምርታዎች የተመዘገቡበት መሆኑን በሚያሳይ መልኩ የአዳባባይ በዓለቱ በልዩ ልዩ ሁነቶች በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል ።
በዐላቶቹ ከመቸውም ጊዜ በበለጠ የኢትዮጵያ መንሰራራት በታወጀበት ወቅት እና በኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት የተገነባው የታላቁ የህዳሴ ግድብ በተመረቀበት ማግስት በመሆኑ ልዩ ደስታና ሞራል በመሰነቅ እንደሚከበርም ታውቋል ።
በቀረበው ሰነድ መነሻነት ስለ በዐሉ አከባበር ተሳታፊዎች አስተያየት የሰጡ ሲሆን አባቶቻችን ያወረሱንን ጀግንነት ሀገራችንን ከውስጥና ከውጪ ባንዳ በመጠበቃ ጭምር ቃል የምንገባበትም ነው ብለዋል ።
እንደ ተቋማችን በተሰበሰበ ገቢ በከተማችን አዲስ አበባ የተሰሩ ልማታዊ ተግባራቶች የከተማ አስተዳደሩ ቃልን በተግባር ያረጋገጠበት በመሆኑ በልዩ ሁኔታ ልናከብረው ይገባል ሲሉ ተናግረዋል
በዓላቱ ለከተማችን ተጨማሪ የገቢ ዕድል ይዞ በመምጣቱ ለተቋማችን ዕቅድ ስኬትም መሠረት በመሆኑ በአግባቡ የበዐላቱን አከባበር ልንጠቀምበት ይገባል ተብሏል ።
የመስቀል ደመራና የኢሬቻ በዓላት ሀይማኖታዊና ባህላዊ የአደባባይ የህዝብ በዓላት በመሆናቸው በቅድመ በዓል እና በበዓል ዕለት ሁላችንም በተቋማችንና በአከባቢያችን በንቃት ልንሳተፍ ይገባል ሲሉ ተሳታፊዎቹ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል
በዓላቱ በዩኔስኮ የማይዳሰሱ ቅርሶች መዝገብ የተመዘገቡ በመሆናቸው ደረጃቸውን በጠበቀና የሀገራችንን መልካም ገጽታ በሚያጎላ መልኩ ተከብረው በሰላም እንዲጠናቀቁ ሁላችንም ሚናችንን መወጣት እንደሚገባ በማጠቃለያ የጋራ ድምዳሜ ተደርሷል