መስከረም 21 / 2018 የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ
በአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ቢሮው የቁጥጥር ስራው በቴክኖሎጂ ማስደገፉ በታክስ ከፋዩ ሕብረተሰብ ዘንድ የፈጠሩት ስሜት በሚመለከት የመርካቶ ነጋዴዎችን አነጋግሯል።
በመርካቶ በጨርቃጨርቅ ዘርፍ ላይ ተሰማሩት የሚሰሩት አቶ ዋቢ ግርግር እና አቶ አስፋው ሐይሌ እንደገለጹት እንደከተማ በከፈሉት ግብር የተሰሩ የልማት ስራዎች ሲያዩ ከፍተኛ የሆነ ደስታ የሚሰማቸው በመግለጽ የቁጥጥር ስራው በዘመናዊ ቴክኖሎጂ እንዲደገፍ ማድረጉ ታክስ ከፋዩ ስራው በግልጸኝነት እንዲሰራ ያስቻለው መሆኑን ገልጸዋል።
አያይዘውም ቢሮ አሰራሩን ዘመናዊ ለማድረግና የታክስ ሕግ ለማስከበር እየሰራቸው የሚገኙ ስራዎች በተለይም ቴክኖሎጂን በመጠቀም የቁጥጥር ባለሙያዎች ማንነታቸውን በቀላሉ ለመለየት የሰራቸው ስራዎች ለአብነት በመጥቀስ አጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል።
በኤሌክትሮኒክስ የንግድ ዘርፍ ተሰማርቶ እየሰራ የሚገኘው ወጣት አልፈሪድ አብድላ እና በስፖርት አልባሳት ንግድ ላይ የተሰማሩት አቶ አክመል ደንድር በበኩላቸው በእረፍት ጊዜያቸው እንደከተማ እየተሰሩ ስራዎች ተዘዋውሮ የማየት ልምድ እንዳላቸው በማውሳት አዲስ አበባ ከሚጠበቀው በላይ እየተለወጠች መሆኑ መሆኑን ገልጸዋል።
ቢሮው አሰራሩ በተለይም የቁጥጥር ስራው በቴክኖሎጂ እንዲደገፍ ማድረጉ የገቢ አሰባሰቡ ውጤታማ ለማድረግ እየሰራቸው የሚገኙ ስራዎች በቢሮውና በታክስ ከፋዩ መካከል ግልጽነትና መተማመን እንዲፈጠሩ የሚያስችሉ ተጠናክረው እንዲቀጥሉም አሳስበዋል።
አያይዘውም ሌብነትና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል ቢሮው በተለይም ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቱ ከነጋዴው ጋር ተቀራርቦ መስራትና ችግሮችን በመወያየት መፍታት እንደሚገባም ጠቁመዋል።
በመርካቶ የቁጥጥርና የታክስ ሕግ ማስከበር ስራዎችን ሲያስተባብሩ ያገኘናቸው በቢሮው የመርካቶ ቁጥር 2 የሕግ ተገዢነት ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ መኮንን ገመች ቢሮው ወይም ቅርንጫፍ የቁጥጥርና ሌሎች የታክስ ሕግን ለማስከበር የሚሰሩ ስራዎች ታክስ ከፋዩን ባሳተፈና የግንዛቤ ስራዎችን ቅድሚያ በመስጠት እየተሰሩ ወይም የሚሰሩ መሆናቸውን ገልጸዋል።
ከቁጥጥር ጋር በተያያዘ ከመርካቶ ግብይት ፈጽመው የሚወጡ ተሽከርካሪዎች የጫኑት እቃ በደረሰኝ ላይ የተመሰረተ ግብይት የተፈጸመባቸው መሆኑን የማረጋገጥ ስራ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።
በተለያየ የሙያ መስክ ብንቀሳቀስም ሁላችን የምንሰራው ለከተማችን ብሎም ለሀገራችን እድገትና ብልጽግና ነው ያሉት ዋና ስራ አስኪያጁ ሌብነትና ብልሹ አሠራሮችን ለመከላከል ከነጋዴው ጋር በቅንጅት እንደሚሰራም ገልጸዋል።
በመጨረሻ በመርካቶ ላይ የተጀመረው የታክስ ሕግ የማስከበር ስራ ውጤታማ ሆኖ ለሌሎች አካባቢዎች አርአያ እንዲሆን የመርካቶ ታክስ ከፋዮች የበኩላቸውን ሚና እንዲጫወቱ አሳስበዋል።