ከአዲስ አበባ የሚወጡ እና የሚገቡ እንዲሁም በከተማዋ ወደተለያዩ አካባቢዎች የሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎች ለጫኑት ዕቃ ህጋዊ ደረሰኝ እንዲቆርጡ የሚካሄድ ቁጥጥር ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገለፀ።
ነሀሴ 25/ 2017 ዓ.ም : አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ወደ ከተማዋ የሚገቡና የሚወጡ እንዲሁም በከተማዋ ከቦታ ወደ ቦታ የሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎች ለጫኑት ጭነት ህጋዊ ደረሰኝ ስለመያዛቸው ቁጥጥር እያደረገ መሆኑን አስታውቋል። የቁጥጥሩን ስራ ሲያስተባብሩ የነበሩት በቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ የታክስ መረጃና የሽያጭ መመዝገቢያ አስተዳደር የስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ አለማየሁ አበራ የቁጥጥሩ ዋና…
