ከተማዋ የምታመነጨውን ገቢ በብቃትና በፍትሃዊነት ለመሰብሰብ እንደሚያስቸል የታመነበት ፕሮጀክት ይፋ ተደረገ፡፡

ከተማዋ የምታመነጨውን ገቢ በብቃትና በፍትሃዊነት ለመሰብሰብ እንደሚያስቸል የታመነበት ፕሮጀክት ይፋ ተደረገ፡፡

የካቲት 11 ቀን 2017ዓም፣ አዲስ አበባ፣ገቢዎች ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ከተማዋ የምታመነጨው ገቢ በውጤታማነትና በፍታዊነት ለማሰባሰብ የሚያስችል ተግባር ሊፈፅም የሚያስችል ፕሮጀክት በመቅረፅ ወደተግባር ሊያሸጋግር መሆኑ ተጠቁሟል።

ቢሮው በዛሬው ዕለት ” መረጃ ማሰባሰብ ላይ መሰረት ያደረገ የገቢ ማሻሻያ ፕሮጀክትን” ለክፍለ ከተማ የታክስ ጉዳይ አመራሮች፣ለወረዳ ዋና ስራ አስፈፃሚዎችንና ለገቢ ፅ/ቤት ኃላፊዎች እንዲሁም ለታክስ ማዕከላት አስተባባሪዎች ይፋ አድርጓል፡፡

የውይይት መድረኩን የመሩት በቢሮው የታክስ ጉዳዮች ዘርፍ ምክትል ኃላፊ ወይዘሮ ወርቅነሽ ሰቦቃ የፕሮጀክቱ ዓላማ የከተማ አስተዳደሩን የገቢ አሠባሠብ የታክስ አስተዳደር ጉዳዮች ከማሻሻል እና የገቢ አሠባሠብ አፈጸጸምን ከማሳለጥ አኳያ የሚገኙትን ጉድለቶች ከመሠረቱ በመለየት አሻጋሪ የገቢ አቅም ማሻሻያ ፕሮጀክት ተግባራዊ ማድረግ መሆኑ ገልፀዋል፡፡

በፕሮጀክቱ በመ፣ረጃ ላይ በመመስረት በሕግ ግብርና ታክስ የመክፈል ግዴታ እያለባቸው ወደ ግብር ስርዓቱ ያልገቡ ተቋማትና ግለሰቦችን ወደ ግብር ስርዓቱ በማስገባት እንዲሁም በግብርና ታክስ ከፋይነት ተመዝግበው ግብራቸውን አሳውቀው የማይከፍሉትን በመለየት ወደ ክፍያ ስርዓቱ በማስገባት የገቢ አፈጻጸሙ እንዲሻሻል እንዲሁም ግብር መክፋል ከሚገባቸው በታች የሚከፍሉ በመለየት በትክክለኛ መረጃ ላይ ተመሰርቶ ግብራቸውን እንዲከፍሉ የማድረግ ግቦች ለማሳካት የሚከናወን መሆኑ ተናግረዋል፡፡

ለዚህ ደግሞ በየደረጃው የሚገኘው አመራር በተለይም ለሕዝብ ቅርብ የሆነው የወረዳ አመራር ሚና ከፍተኛ መሆኑን በማውሳት ቢሮ የግብር አሰባሰብ ሒደቱ በጠራ መረጃ ላይ ለማድረግ ያቀደውን የመረጃ አሰባሰብ ስራ ውጤታማ እንዲሆን የበኩሉን ሚና ሊወጣ ይገባል።

በማበልጸጊያ ሰነዱ ከቢሮ ኃላፊው ጀምሮ በየደረጃው የሚገኘው መዋቅር / ኮሚቴ ኃላፊነት በዝርዝር መቀመጡን የገለፁት በቢሮ የገቢ አወሳሰንና አሰባሰብ ዳይሬክተር አቶ ወንድማገኝ ካሳይ በመረጃ አሰባሰብ ሒደቱ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ቢሮ ጋር በመተባበር 1 ሺህ የሚደርሱ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች እንደሚሳተፉ እና የመረጃ ማሰባሰቡ በ45 ቀናት ውስጥ እንደሚጠናቀቅ ሰነዱን ባቀረቡበት ወቅት ገልጸዋል።

በመድረኩ ተሳታፊ የሆኑ የወረዳ አመራሮችና የክፍለ ከተማ የታክስ ጉዳዮች ም/ስራአስኪያጆች በፕሮጀክቱ ትግበራ ላይ አስተያየቶችና ጥያቄዎች ያቀረቡ ሲሆን በጥናት ቡድኑ አባላትና በቢሮው አመራሮች ምላሽና ማብራሪ ተሰጥቷ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *