የከተማዋ የገቢ ግብረ ኃይል የ2018 በጀት ዓመት የሀምሌ ወር የገቢ ዕቅድ አፈፃፀም ላይ ውይይት በማካሄድ ቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀመጠ ።

ነሀሴ 18 / 2017ዓ.ም፣ አዲስ አበባ፣ ገቢዎች ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የገቢ ግብረ ኃይል በ2018 በጀት ዓመት በሀምሌ ወር ዕቅድ አፈፃፀም ላይ ወይይት አካሄዷል፡፡

መድረኩን የመሩት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊና የገቢ ግብረ ኃይል ም/ሰብሳቢ አቶ አብዱላቃድር ሬድዋን የበጀት ዓመቱ የሀምሌ ወር የገቢ አፈፃፀም አበረታች ነው ብለዋል፡፡

በዚህም በ2018 በጀት ዓመት በሀምሌ ወር በከተማ ደረጃ 26 ነጥብ 54 ቢሊዮን ለመሰብሰብ ታቅዶ 26 ነጥብ 24 ቢሊዮን ወይም የዕቅዱን 98 ነጥብ 8% በመሰብሰብ ለማሳካት መቻሉ በመድረኩ ተጠቁሟል፡፡

ቅንጅታዊ አሰራር ለገቢ አሰባሰብ ወሳኝ መሆኑን የገለፁት አቶ አብዱልቃድር የከተማዋ የልማት ስራዎች ቀጣይነት ለማረጋገጥ የገቢ አሰባሰብ ተቋማት ተግባራትን በቅንጅት መምራት አለባቸውም ብለዋል፡፡

ሀላፊው አክለውም የበጀት ዓመቱን ዕቅድ በተሟላ መልኩ ለማሳካት የማዕከል ገቢ ሰብሳቢ ተቋማት የራሳቸውን የገቢ ዕቅድ ለማሳካት ራሱን የቻለ የገቢ ማስፈፀሚያ ዕቅድ በዝርዝር በማዘጋጀት አፈፃፀሞችን በመገምገም በአግባቡ መምራት ይጠበቅባቸዋልም ብለዋል፡፡

በመጨረሻም በከተማዋ እየተካሄዱ ያሉ ሁሉን አቀፍ የልማት ስራዎች ፣ የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፀፃፀም እንዲሁም የ2018 በጀት ዓመት የሀምሌ ወር አፈፃፀም እንደከተማ በበጀት ዓመቱ የታቀደውን የ350 ቢሊዮን ብር የገቢ ዕቅድ ለማሳካት የሚያስችል አቅም እንዳለም አመላካች መሆኑን አስረድተዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *