መስከረም 5/ 2015 ዓ. ም : አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በዛሬው ዕለት የወርቃማ ሰኞ የልምድ ልውውት መድረክ ተካሄደ፡፡
በመድረኩ የቢሮው የዕዳ ክትትልና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ንብረት በሪሁን ልምዳቸውን አካፍለዋል፡፡
ለመድረኩ ተሳታዎች ለዓላማ መኖር፣ የሚገጥሙ ፈተናዎችንና ችግሮች በማለፍ ግብ ማሳካት፣በተሰማሩበት የስራ ዘርፍ ችግር ፈቺ ሃሳቦችን ማመንጨትና ስራን መውደድ ለስኬት የሚያበቁ መንገዶች መሆናቸው ካለፉበት የህይወት ተሞክሮ በመቅዳት ልምዳቸውን አጋርተዋል።