በቢሮው የአገልግሎት አሰጣጥ መማክርት ጉባዔ ተቋቋመ ።

ጥቅምት 15 / 2018 ዓ.ም አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በሚሠጠው አገልግሎት እርካታን ማረጋገጥ ይቻል ዘንድ የአገልግሎት አሰጣጥ መማክርት ጉባዔን በዛሬው ዕለት አቋቁሟል።

በዚህ የመማክርት ጉባኤ ምስረታ ላይ 50 የሚሆኑ ከንግድ ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፣ ከሲቪክ ማህበራት፣ ከንግድ ማህበረሰብ ፣ ከተገልጋይ ፣ ከባለድርሻ አካላት ሴክተር ተቋማት ፣ ከገቢዎች ቢሮ እና ሌሎችም ተወካዬች ተገኝተዋል ።

እነዚህም የመማክርት ጉባኤው ጠቅላላ አባላት ሆነው የሚቀጥሉ ሲሆን ከጠቅላላ አባላቱ ውስጥ ሰብሳቢ ፣ ምክትል ሰብሳቢና ፀሀፊን ጨምሮ 7 የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴዎችን በጠቅላላ ዓባላቱ ምርጫ እና ይሁንታ በመምረጥ አፅድቀዋል።

መድረኩን የመሩት የቢሮው የሞደርናይዜሽን ዘርፍ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ መሐመድ አብዱርሃማን ባስተላለፉት መልዕክት ” በመንግስት ተቋማት የሚሰጡ አገልግሎቶችን ማሻሻል የሚቻለው ከተቋማቱ ጥረት በተጨማሪ የሲቪክ ማህበራት፣ የንግዱ ማህበረሰብ ፣ባለድርሻ አካላትና ተገልጋዮችን በማሳተፍ መሆኑን ጠቁመው የተገልጋይን እርካታ ለማረጋገጥ ሁሉም አካል የድርሻውን እንዲወጣ ማስቻል ቁልፍ ሚና አለው ብለዋል ።

ሀላፊው አያይዘውም የቢሮው የመማክርት ጉባኤ አባላትና አመራር በቀጣይ በበጀት አመቱ ሩብ አመት የተከናወኑ የአገልግሎት አሰጣጥን በጥልቀት በመገምገምና ውይይት በማድረግ የቀጣይ አቅጣጫዎችን እንደሚያስቀምጥ አመላክተዋል ።

የአገልግሎት አሰጣጥ መማክርት ጉባኤ የሚያከናውናቸውን ዋና ዋና ተግባራትንና የመማክርት ጉባኤ አባላት አደረጃጀት የሚያሳይ ሰነድ በአቶ ግርማ አለሙ በቢሮው የስታንዳርዳይዜሽንና የአገልግሎት አሰጣጥ ክትትልና ድጋፍ ዳይሬክተር ለተሳታፊዎች ቀርቦ ሰፊ ውይይትና ማብራሪያ ተካሂዷል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *