የታክስ ባለስልጣኑ ግብራቸውን አሳውቀው ያልከፈሉ ግብር ከፋዮች በቀሪዎቹ ጥቂት ቀናቶች ግብራቸውን አሳውቀው በመክፈል የዜግነት ግዴታቸውን እንዲወጡ ጥሪ ማቅረቡ ተገለፀ ።

ጥቅምት 28 /2018 ዓ.ም አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የግብር ከፋዮች ዓመታዊ ግብር አሳውቆ የመክፈያ ጊዜ እየተጠናቀቀ በመሆኑ በከተማዋ ያሉ ግብር ከፋዮች ግብራቸውን በሚከፍሉበት ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቶች በመገኘት በቀሪ ቀናት በመክፈል የግብር መክፈል ኃላፊነታቸዉን እንዲወጡ አሳሰበ

ቢሮው ለግብር ከፋዮች ምቹ ፣ ቀልጣፋና ፈጣን የሆኑ አሰራሮችን ዘርግቶ ሲያስተናግድ ቢቆይም የ2017 በጀት ዓመት ዓመታዊ የንግድ ትርፍ ገቢ ግብር ማሳወቂያ ጊዜ 2 ቀናት ብቻ የቀሩት በመሆኑ የማሳወቂያ ጊዜው ከመጠናቀቁ በፊትና በመጨረሻ ቀናት ከሚገጥም አላስፈላጊ ወረፋ፣ እንግልት፣ የሲስተም መጨናነቅ እንዲሁም ከአላስፈላጊ ቅጣት ለመዳን ከወዲሁ ግብርዎን አሳውቀው በመክፈል የዜግነት ግዴታዎን እንዲወጡ ሲል ቢሮው አሁንም ጥሪ አቅርቧል ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *