ህዳር 17 ቀን፤2018፣ አዲስ አበባ፣ገቢዎች ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት አራት ወራት በ5 ሺህ 203 የደረቅ ጭነት ተሸከርካሪዎች ላይ የደረሰኝ ቁጥጥር ማካሄዱ ተገልፆል፡፡
የደረሰኝ ቁጥጥሩ በሁሉም የከተማዋ አቅጣጫዎች ወደ ከተማዋ በሚገቡ፣ከከተማዋ በሚወጡና በከተማዋ ውስጥ በሚንቀሳቀሱ የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪዎች ፣ሚኒባሶችና አነስተኛ ሽፍን መኪኖች ላይ ነው የተካሄደው፡፡
በዚህም ያለደረሰኝ ጭነት በመያዝ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 907 የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪዎች በቁጥጥር የዋሉ ሲሆን 1 ሺህ 39 ግብር ከፋዮች ደረሰኝ እንዲቆርጡ 997 ግብር ከፋዮች ላይ ደግሞ አስተዳደራዊ እርምጃ እንዲወሰድ ተደርጓል ተብሏል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ በተደረገው የቁጥጥር የደረቅ ጭነት ተሸከርካሪዎቹ የጫኗቸው ሸቀጦች ላይ የ954 ሚሊዮን 803 ሺህ ብር ደረሰኝ እንዲቆረጥባቸው ለማድረግም መቻሉ ተገልፃል፡፡
በአሁኑ ወቅትም የደረሰኝ ቁጥጥሩ በቀን ብቻም ሳይሆን በለሊት ጭምር ተጠናክሮ መቀጠሉ የተገለፀ ሲሆን ደረሰኝ ሳይዙ ሸቀጦች በመጫን በሚንቀሳቀሱ ተሸከርካሪዎች ላይ ከሚወሰድ አስተዳደራዊ እርምጃ በተጨማሪ በቀጣይ የደረቅ ጭነት አሽከርካሪዎቻቸው ላይም የህግ ተጠያቂነት እንዲሰፍን የሚደረግ መሆኑ አብራርቷል።
