የካቲት 11/ 06 / 2018 ዓ / ም የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ
በአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ በየደረጃው ለሚገኙ ባለሙያዎች በሲግታስ (SIGTAS) አተገባበር ላይ ሙያዊ ስልጠና በመስጠት ላይ ይገኛል።
በስልጠና መድረኩ የቢሮው የታክስ ጉዳዮች ዘርፍ ምክትል ኃላፊ ወይዘሮ ወርቅነሽ ሰቦቃ በበጀት ዓመቱ በከተማ ደረጃ 350 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ ወደተግባር መግባቱን አስታውሰዋል።
አክለውም በበጀት ዓመቱ የታቀደው የገቢ ዕቅድ ለማሳካት የአሰራር፣የአደረጃጀት፣የቴክኖሎጂ ልማቴና የሰው ኃይል ግንባታ የሪፎርም ተግባራት ወደተግባር ማሸጋገሩ ተናግረዋል።
ከሰው ኃይል ግንባታ አኳያም በየደረጃው ያሉ አመራሮችና ፈጻሚዎች ከሌብነትና ብልሹ አሰራሮች በመራቅ ፍትሐዊና ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲሰጡ የሚያስችሉ ስልጠናዎች በማዘጋጀት በተከታታይ እየተሰጠ መሆኑም አብራርተዋል።
በመጨረሻም በሰልጠና መድረኩ የተሳተፉ ባለሙያውች የከተማው እድገት በተሰበሰበው ገቢ ላይ እንደሚመሰረት በመገንዘብ ከቴክኖሎጂ ጋር መላመድ፣ ለታክስ ከፋዮች በአክብሮት አገልግሎት መስጠት እንደሚገባቸው አሳስበዋል።
ፍትሃዊ የገቢ አሰባሰብ ለአዲስ አበባ ሁለንተናዊ ብልፅግና!
ቢሮው የቴክኖሎጂ አጠቃቀሙን በማጎልበት ፍትሃዊና ዘመናዊ የግብር አሰባሰብ ስርዓት ለማጎልበት በትኩረት እየሰራ መሆኑ ተገለፀ።
